Get Mystery Box with random crypto!

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከናወነ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውጤታማ በመሆኑ በአብዛኛው የሀ | YeneTube

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከናወነ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውጤታማ በመሆኑ በአብዛኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ መምጣቱን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች፣ በሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እና በመደበኛ የመንግስት የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ መግለጫ እየሰጡ ነው፡፡የሰላም እና የደህንነት ሁኔታዎችን በተመለከተ በተሰጠው መግለጫ ጽንፈኝነትና ፖለቲካዊ ገጽታ ባላቸው መገፋፋቶች ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶችን የሰው ሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት የህብረተሰቡን ደህንነት እና ሁለንተናዊ ሀገራዊ አንድነትን ለማስከበር እየተወሰደ ያለው ህብረተሰብን ያሳተፈ የተቀናጀ እርምጃ በሁሉም ክልሎች ሊባል በሚችል መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡

በህብረተሰብ ንቅናቄ እና ድጋፍ ታጅቦ እየተካሄደ የሚገኘው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ውጤታማ እየሆነ በመምጣቱ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ መምጣቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።እየተደረጉ ባሉ ሥራዎች በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

በጎንደር በቀብር ስፍራ በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተከሰተ አለመግባባት የተፈጠረውን ግጭት ለማስፋፋት የተደረገው ሙከራ በሰላም ወዳዱ የህብረተሰብ ክፍል እና የጸጥታ ኃይሎች የተቀናጀ ርብርብ መለስተኛ ጉዳት ቢያስከትልም ሴራው ግን ከሽፏ ብለዋል፡፡በኦሮሚያ ክልል በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው የተቀናጀ ዘመቻም ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው ያመለከቱት።ዘመቻው በፀረ ሽብርና በፀረ ሽብር ዘመቻ ኮማንዶ የታገዘ በመሆኑ ከፍተኛ ውጤት እየመጣ ነው ብለዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa