Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው አሰራጭተዋል ብሎ የተጠረጠራ | YeneTube

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው አሰራጭተዋል ብሎ የተጠረጠራቸውን የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር ጨምሮ 4 አባላቱን አገደ፡፡

በፓርቲው የሥራ ኃላፊዎችና በአባላቱ ላይ እግድ የጣለው የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ነው፡፡ግለሰቦቹ የሳምንት ሥራ መከታተያ ቅፅ በሚል ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው ግንቦት 2፣ 2014 በብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የዋትስ አፕ ግሩፕ ላይ በመላክ ተጠናክረው መታገዳቸው ሸገር ከፓርቲው ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውም ከትናንት በስትያ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳዩ ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ሰነዱ ፍፁም ስህተት እና የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሂደት ዲሞክራሲያዊነትን የሚያቀጭጭ ብሎታል በውሳኔው፡፡በመሆኑም ሰነዱን አዘጋጅተዋል ተብለው የተጠረጠሩት 4 የፓርቲው አባላት በሰነዱ ላይ ያላቸውን ተሳትፎና የህግ ጥሰታቸው ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለፓርቲው ህገ ደንብ ትርጉምና ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተመርቷል ተብሏል፡፡

ጉዳዩ በኮሚቴው ተመርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስም ፡-

• የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊው አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ
• የፋይናንስ መምሪያ ሀላፊው አቶ አንድነት ሽፈራሁ
• የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደና
• አባል የሆኑት አቶ ኢዮብ መሳፍንት ከሀላፊነታቸው ለጊዜው እንዲታገዱ መወሰኑን ሸገር ራዲዮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa