Get Mystery Box with random crypto!

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የዩኤኢ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ! ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አ | YeneTube

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የዩኤኢ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ!

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡የአቡ ዳቢው ልዑል አልጋ ወራሽ፤ ወንድማቸው ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ ትናንት አርብ ማረፋቸውን ተከትሎ ነው የዩኤኢ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት፡፡የሃገሪቱ ጠቅላይ ምክር ቤት ነው ሼክ መሃመድን ፕሬዝዳንት አድርጎ የመረጠው፡፡ ሼክ መሃመድ ምክር ቤቱ እምነት አድሮበት ለሰጣቸው ትልቅ ኃላፊነት አመስግነዋል፡፡ሼክ መሃመድ የዩኤኢ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa