Get Mystery Box with random crypto!

የመንግሥት የፕሮፎርማ ግዥ ከመጪው በጀት ዓመት አንስቶ በግዥ ካርድ ሊሆን ነው! የፌዴራል በጀት | YeneTube

የመንግሥት የፕሮፎርማ ግዥ ከመጪው በጀት ዓመት አንስቶ በግዥ ካርድ ሊሆን ነው!

የፌዴራል በጀት ተጠቃሚ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከመጪው በጀት ዓመት አንስቶ የፕሮፎርማ ግዥ የሚፈጽሙት፣ መንግሥት ባዘጋጀው የግዥ ካርድ ሊሆን ነው፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሰኔ ወር ጀምሮ የግዥ ካርዱን ወደ ሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ማሠራጨት የሚጀምር ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዕቃ አቅራቢዎች የክፍያ መሣሪያ (POS Machine) በነፃ ያቀርባል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋራ ያዘጋጁት የመንግሥት ግዥ ካርድ፣ ባንኩ በመሥሪያ ቤቱ ስም የሚያዘጋጀውና በፕሮፎርማ ለሚፈጸሙ ወይም ሌሎች ጥቃቅን ግዥዎች የሚውል ነው፡፡ ይህ ካርድ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር ሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የፕሮፎርማ ግዥዎችን የሚፈጽሙት በግዥ ካርድ ብቻ እንደሚሆን፣ በገንዘብ ሚኒስቴር የትሬዠሪ ዳይሬክተር ወ/ሮ ነጠሩ ወንድወሰን ተናግረዋል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa