Get Mystery Box with random crypto!

ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው ገለጸ! በትግራይ ክልልና በፌደራል | YeneTube

ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው ገለጸ!

በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።የነዚህ ውጥረቶች መባባስና ይህንንም የሚያጋግሉ ትርክቶች በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋትን ደቅኗል ብሏል ኢሰመኮ በዛሬው ዕለት ግንቦት 7፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ።

በተለይም አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ ሌላ ጦርነትም ሆነ ግጭት መሸከም እንደማትችል አፅንኦት ሰጥቷል።ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣው የዋጋ ግሽበት ፣ የመሠረታዊ አቅርቦቶች እጥረትና ከሰሜን ኢትዮጵያ ሰፊ አካባቢዎች የሚደረጉ የምርት እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸው፣ እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ሰብዓዊ ፍላጎቶችም የሃገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን በእጅጉ ጎድተውታል ብሏል።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ቀጣይ ግጭት እና ጦርነት የሚያስከፍለው በዋጋ የማይገመት ነው ያለው መግለጫው ሲቪል ህዝቦችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ እና ተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ ህግ ጥሰቶችን እንደሚያስከትልም አጽንኦት ሰጥቷል።

በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ ኃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ለአስራ ስምንት ወራት የዘለቀው ጦርነት መቋጫ ሊሆን ይችላል የሚል ተስፋን ዘርቶ የነበረ ቢሆንም ከሰሞኑ ዳግም ጦርነት ይከሰት ይሆን የሚሉ ፍንጮች ጥያቄ ፈጥረዋል።

ሙሉ ዘገባው: https://bbc.in/3woveHL

@YeneTube @FikerAssefa