Get Mystery Box with random crypto!

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ከአፋር ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እራሱን አገለለ! የአፋር ሕዝብ ፓ | YeneTube

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ከአፋር ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እራሱን አገለለ!

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ የአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያልተሳተፍኩበትና ከአቋሜ የሚጻረር መግለጫ በማውጣቱ እራሴን ከምክር ቤቱ አግልያለሁ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለለጫ አስታውቋል፡፡

የአፋር ህዝብ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤቱ አባል በመሆን እየተንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣ ጉዳዩ ከአብሮነት ወደ ግለኝነት ያዘነበሉ አካሄዶችን ላለፉት ሦስት ዓመታት ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡ ምክር ቤቱ በግልጽ የህዝብን ስብራቶች በመደበቅ ላይ የተሰማራ በመሆኑ፤ ከጋራ ምክርቤቱ ጋር በዚህ መልኩ መቀጠል ለአፋር ሕዝብና ለፓርቲው ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዘነ መሆኑን ተመልክቻለሁ ብሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa