Get Mystery Box with random crypto!

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ! የገን | YeneTube

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ!

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኦስማን ዲዬ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

ገንዘቡ ለአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት እንዲሁም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡በዚህም 210 ሚሊዮን ዶላሩ በአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት የሚውል ሲሆን ቀሪው ደግሞ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ይውላል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa