Get Mystery Box with random crypto!

1ሺሕ 127 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ! በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎች | YeneTube

1ሺሕ 127 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ!

በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺሕ 127 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከተመላሾቹ መካከል ስድስት ህጻናትና 1 ሺሕ 121 ወንዶች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው 38 ሺሕ 853 ኢትዮጵያዊያንን መመለስ ተችሏል ተብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa