Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ከ12,000 ለሚበልጡ ምርቶችና አገልግሎቶች ደረጃ የተዘጋጀ ቢሆንም ብዙዎቹ ግን በሰዉ | YeneTube

በኢትዮጵያ ከ12,000 ለሚበልጡ ምርቶችና አገልግሎቶች ደረጃ የተዘጋጀ ቢሆንም ብዙዎቹ ግን በሰዉ ዘንድ አይታወቁም ተባለ፡፡

የወጡ ደረጃዎች አለመታወቅ ደግሞ ምርቶችና አገልግሎቶች የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ስለማሟላት አለማሟላታቸው ለማረጋገጥ የሚከወነውን ስራ አስቸጋሪ እንዳደረገው ተነግሯል፡፡የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት በደረጃ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አሰናድቶ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ተመክሮበታል፡፡

የኢንስትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ እንዳሉት ከተዘጋጁት ደረጃዎች 296ቱ አስገዳጅ ናቸው፡፡የተቀሩትና የሚበዙት ደግሞ አስገዳጅ ያልሆኑ ደረጃዎች ናቸው ብለዋል፡፡

አስገዳጅ የሆኑትም ሆኑ ያልሆኑት ግን ብዙ በሰዉ ዘንድ እንደማይታወቁ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡በመድረኩ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ እንዳለው መኮንን በበኩላቸው በኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ንግድ መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ አንዱ መንገድ የወጡ ደረጃዎችን ጠብቆ ማምረት ነው ብለዋል፡፡

ጥራትና ደረጃ የአገርን ገፅታ የሚወስኑ ጉዳዮች እንደሆኑ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡መንግስት ምርቶችና አገልግሎቶች የተዘጋጀላቸውን ደረጃ አሟልተው እንዲገኙ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡ከጊዜው ጋር የሚሄዱ የፍተሻ መሳሪያዎች እንዲሟሉና ዘመናዊ ማዕከላት እንዲገነቡ ከፍተኛ ገንዘብ የመደበው በዚሁ ምክንያት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa