Get Mystery Box with random crypto!

#ሰርድዮን_አዲስ_መጽሐፍ #ሉባር_3ኛ_ዕትም በገበያ ላይ! =============== | YeneTube

#ሰርድዮን_አዲስ_መጽሐፍ
#ሉባር_3ኛ_ዕትም
በገበያ ላይ!
================
ደራሲ መምህር በረደድ ገዳሙ ከዚህ በፊት ሉባር በተሰኘ ተወዳጅ ድርሰቱ የምናውቀው ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ የምስጢራት ሰረገላ የሆነውንና በርካታ የተደበቁ የሀገራችን ጥንታዊ ጥበብና ምስጢራትን ሳይንሳዊ በሆነ ቅኝት ፍለጋ የተካሄደበትን ሰርድዮን የተሰኘውን ሁለተኛ ድርሰቱን ይዞልን መጥቷል።

ደራሲው በሉባር የጀመረውን ረቂቅ ምስጢር ፍለጋ በሰርድዮን ወደ ዲማ ጊዮርጊስ ተመልሶ፦ ከዲማ ጊዮርጊስ እስከ ደብረ ገነት ሰይፍአጥራ ማርያም፤ ከደብረ ገነት ሰይፍአጥራ ማርያም እስከ አስመራ እንዳ ማርያም ብሎም እስከ ዳህላክ ደሴት ድረስ በዘረጋው መሳጭ መቼቱ በየደረሰበት ሁሉ ታሪክንና ምስጢርን በገፀባህሪያቱ በኩል በሚጣፍጥ ሁኔታ እንደዥረት አፍስሶ በመጨረሻም በሉባር የጀመረውን የሦስቱን እንክብሎች ምስጢር እና ሀገራዊ ምስጢራትን ከብዙ እልህ አስጨራሽ ፍለጋና ድካም በኋላ በግዮን ወንዝ አናት ላይ እንዲፈቱ አድርጓል፡፡
===
#በምሁራን_ከተሰጠ_አስተያየት_መካከል

<<ሰርድዮን የሉባር መጽሐፍ ቀጣይ ክፍል ነው፡፡ በዚህ ስራ በአማርኛ ሥነጽሑፍ ታሪክ ራሳቸውን ችለው የተሟላ ሀሳብ ማስተላለፍ የሚችሉ የተለያዩ ድርሰቶችን በታሪክ በማስተሳሰር ማቅረብ በደራሲ ብርሃኑ ዘርይሁን ማእበሎች ተጀመረ እንጅ የቀጠለ አይመስለኝም፡፡ ሉባር እና ሰርድዮን እንደማእበሎች ናቸው፡፡››

ዶ/ር ሞገስ ሚካኤል
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ የዐባይ የቋንቋና የባህል ጥናት ተቋም ኃላፊ
====
በየመጽሐፍ መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ማግኘት ይችላሉ።

Telegram-
https://t.me/teklu_tilahun