Get Mystery Box with random crypto!

የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በዜጎች ላይ ያልተመጣጠነ እርምጃ መወሰዳቸውን ኢሰመኮ ገለጸ! በጋ | YeneTube

የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በዜጎች ላይ ያልተመጣጠነ እርምጃ መወሰዳቸውን ኢሰመኮ ገለጸ!

በጋምቤላ ከተማ በዜጎች ላይ ያልተመጣጠነ እርምጃ መወሰዱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ገለጸ፡፡ኢሰመኮ መምሻውን ባሳለፍነው ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ ከተፈጠረው ጉዳይ ጋር ተያይዞ እየተከሰቱ ባሉ ድርጊት ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል፡፡ድርጅቱ እንዳለው ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ምክንያት ነዋሪዎች ከሕግ ውጭ ግድያ ስለመፈጸሙ መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡

በተለይም በጥቃቱ ተሳትፈዋል ወይም ተባብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ቤት ለቤት በመሄድ ጭምር ግድያዎች እንደተፈጸሙ ኢሰመኮ ከምስክሮችና የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃዎች ጭምር ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን አስታውቋል።የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሰዎችን ደኅንነትና የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ የመንግስት ቀዳሚው ተግባር መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ የሰብአዊ መብቶች መርሆች ሊከተሉ እንደሚገባ ያሳሰቡት ዶ/ር ዳንኤል በተለይም የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥም አሳስበዋል።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa