Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube Y
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
Digitalliteracy
Mastercardfoundation
Educationinnovation
Shegamedia
Technologyineducation
Edtechmondaysethiopia
Edtechethiopia
Jointheconversation
Equityineducation
All tags
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
Digitalliteracy
Mastercardfoundation
Educationinnovation
Shegamedia
Technologyineducation
Edtechmondaysethiopia
Edtechethiopia
Jointheconversation
Equityineducation
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 128.55K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-01 10:45:32 የአውሮፓ ህብረት የጣለውን ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ውሳኔ እንዲያጤነው ኢትዮጵያ ጠየቀች!

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት በህገወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ ነው በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ አስታወቀች።የአውሮፓ ህብረት ይህንን አቋሙን እንዲያጤነው በቤልጂየም፣ ብራስልስ ተቀማጭነቱን ያደረገው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት ሚያዝያ 22/ 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት (ካውንስል) ያስተላለፈው የእግድ ውሳኔ በህብረቱ አባል አገራት ለመኖር ህጋዊ ፍቃድ የተነፈጋቸው ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በክብር፣ በስርዓት እና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ እንዲመለሱ ለማድረግ ሁለቱ ወገኖች በቅርበት እየሰሩ ባለበት ወቅት ነው ሲልም መግለጫው አስፍሯል።የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ከሰሞኑ በኅብረቱ ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ መደረጉን አስታውቋል።

በዚህ ዕገዳ መሠረት፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም።ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉየዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም።

በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።ለዚህም ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ገልጾ “የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዜጎችን መልሶ ለመውሰድ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም” ብሏል።ኢትዮጵያ በበኩሏ በሰጠችው ምላሽ ጊዜያዊ የቪዛ እግዱ ዜጎቿን ወደ አገራቸው ለመመለስ እና ከማህበረሰቡም ጋር መልሶ ለማዋሃድ በኢትዮጵያ እና በህብረቱ መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር ያላገናዘበ ነው ብላለች።

በተጨማሪም ውሳኔው ማንነትን ለማረጋጋጥ የሚደረገውን አድካሚ ሂደት ከግምት ውስጥ ማስገባት አልቻለም ሲል ኤምባሲው ተችቶታል።የምክር ቤቱ እርምጃ "ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከህብረቱ አባላት አገራት ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን የቅበላ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራዊ እርምጃዎች ላይ እንቅፋት የሚፈጥር ነው ብሏል ከቤልጂየም በተጨማሪ ለሉክሰምበርግ ፣ ኔዘርላንድስ እና የአውሮፓ ህብረት የሚያገለግለው ኤምባሲው።

የአውሮፓ ህብረት አቋሙን እንደገና እንዲያጤን የጠየቀው ኤምባሲው ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከአውሮፓ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን አሰራር በተመለከተ ከተሰጠው ውሳኔ ጋር በሚጣጣሙ እርምጃዎች ላይ ይመክራል ብሏል።ህብረቱ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ የጉዞ ሰነዶች በመስጠት እንዲሁም በፍቃድ እና ያለ ፈቃድም የሚደረግ ስደተኞችን የመመለስ ሂደትን በተመለከተም ኢትዮጵያ “በቂ ትብብር አላደረገችም” ብሎ ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
12.6K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-30 18:01:27
እንግሊዝ በዚህ ዓመት በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ልታሸጋግር ነው!

የእንግሊዝ መንግስት በያዝነው የአውሮፓውኑ 2024 ቁጥራቸው 6,000 የሚሆን ስደተኞችን ‘ወደ ሩዋንዳ ያሸጋግራል’ ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ።እንግሊዝ ወደ ሩዋንዳ የምትልካቸውን ስደተኞች የሚመለከተው ይህ አሃዝ ይፋ የተደረገው ሰሜናዊ አውሮፓን በአነስተኛ ጀልባዎች አቋርጠው የሚመጡትን ስደተኞች ሙከራ ለማስቆም የተያዘው ውጥን ለወራት ከዘለቀ የፓርላማ ውዝግብ በኋላ ጽድቆ የሃገሪቱ ሕግ በሆነ ቀናት ዕድሜ ውስጥ ነው።

የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ሩዋንዳ በአሁኑ ወቅት እንግሊዝ ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 5,700 የሚደርሱ ስደተኞችን ለመቀበል “በመርህ ደረጃ” ተስማምታለች ሲል የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ከእነኚም መካከል 2,143 የሚሆኑት ወደሩዋንዳ ከመላካቸው አስቀድሞ "እስር ላይ ሊቆዩ መቻላቸውን" የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ አክሎ አመልክቷል።

የእንግሊዝ የጤና ሚንስትር ቪክቶሪያ አትኪንስ በበኩላቸው የሕግ አስፈጻሚ አካላት ቀሪውን ካሉበት ፈልገው ያመጣሉ ብለዋል አያይዘውም ማንኛውም ስደተኛ በደንቡ መሰረት መጥቶ ካልተመዘገበ ካለበት ተይዞ ይቀርባል’ ብለዋል።ባለስልጣናቱ የመንግስት አኃዛዊ መረጃዎችን ጠቅሰው እንዳመለከቱት ባለፉት 18 ወራት ጊዜ ውስጥ በትናንሽ ጀልባዎች ተሳፍረው የእንግሊዝ ቻናልን ለማቋረጥ የሞከሩ ቁጥራቸው ከ57, 000 በላይ ፍልሰተኞች ከዚያች አገር ዘልቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
13.5K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-30 14:53:53
የአብን አባሉ አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከአማራ ክልል የመንግሥት ኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡

ላለፈው ሁለት ዓመት ከስምንት ወር ገደማ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን (አባሉ) አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ካባለፉት “ሶስት፣ አራት ወራት” ወዲህ አንስቶ ከኃላፊነት የመልቀቅ ጉዳይ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር “በዝርዝር” ንግግር ማድረጋቸውን ያስታወሱት አቶ ጣሂር፤ የክልሉ መንግሥት ጥያቄውን እንደተቀበለው ገልጸዋል።የቀድሞው የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ፤ “ትንሽ የቤተሰብ ጉዳይ ስለነበረብኝ በቤተሰብ እና በራሴ ጉዳይ ነው የለቀቅሁት” ሲሉ ከኃላፊነት የለቀቁበትን ምክንያት አስረድተዋል።

አቶ ጣሂር፤ “[ከክልሉ አመራሮች ጋር[ በመነጋገር ከፓርቲያችን ሰው ተክተን ነው የወጣሁት” ሲሉም ከኃላፊነት ሲለቅቁ በእሳቸው ቦታ የሚሾም ሌላ የፓርቲው አባል እንዲተካ መደረጉን ገልጸዋል።በአቶ ጣሂር ቦታ ሌላኛው የአብን አባል አቶ መልካሙ ፀጋዬ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሾማቸውን የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
14.0K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-30 12:23:20 ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው ስደተኛ በአሜሪካ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸናፊ ሆነ!

ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው የላኦስ ተወላጁ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ ጃክፖት አሸናፊ ሆነ።የ46 ዓመቱ ቼንግ ሳፋን ፓወርቦል በተሰኘው የሎተሪ ጃክፖት ጨዋታዎች እድለኛ መሆኑን የውድድሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል።ቼንግ ዕድለኛ ያደረገውን የሎተሪ ቲኬት የገዛው በኦሪጎን ግዛት በፖርትላንድ ከተማ ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር።ግለሰቡ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ግብር ተቀንሶ 422 ሚሊዮን ዶላር ያህል የሚደርሰው ሲሆን ይህንንም ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር እኩል እንደሚካፈሉ አስታውቋል።

“አሁን ቤተሰቤን አንበሻብሻለሁ። ለራሴም ጥሩ ዶክተር መቅጠር እችላለሁ” ሲል አስረድቷል።“ህይወቴ ተቀይሯል” ሲል ለሲቢኤስ አጋር የሆነው ኮይን የተናረው ቼንግ አምላኩ እንዲረዳው በጸሎት መማጸኑን አስረድቷል።ቼንግ አክሎም ለቤተሰቡ ሲያልሙት የነበረውን ቤት መግዛት እንደሚፈልግ እና ፓወርቦል የሎተሪ ጃክፖት መጫወቱን እንደሚቀጥል ተናግሯል።“እንደገና እድለኛ ልሆን እችላለሁ” ሲል ተስፋውን አስረድቷል።

ሲቢሲኤስ በአሜሪካ ውስጥ የቢቢሲ የሚዲያ አጋር ነው።ላለፉት ስምንት ዓመታት በኬሞቴራፒ ህክምና ውስጥ ያለው ቼንግ ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር በመተባበር ከ20 በላይ የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶችን መግዛታቸውን ተናግሯል።የሎተሪ ቲኬቶቹ አሸናፊ ቁጥሮች 22፣ 27፣ 44፣ 52፣ 69 እና ቀይ ፓወርቦል 9 ነበሩ ተብሏል።

በፓወርቦል ታሪክ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የገንዘብ ሽልማት መሆኑ የተነገረ ሲሆን እስካሁን ድረስ በከፍተኛ ደረጃ የተቀመጠው በ2022 አሸናፊ የነበረው የ2.04 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት ነው።የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶች በ45 አሜሪካ ግዛቶች፣ በኮሎምቢያ እንዲሁም በፖርቶ ሪኮ እና በአሜሪካ የቨርጂን ደሴቶች እያንዳንዳቸው በ2 ዶላር ነው የሚሸጡት።የሎተሪ ቲኬቶች ዋጋ መጨመሩ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የቢሊዮን ዶላር ሽልማቶች በጣም የተለመዱ ሆነዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
14.2K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-30 12:23:04
13.6K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 21:34:02 ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በሁለት ወራት ገደማ የመጨረሻውን ሥምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል!

ለሶማሌላንድ እውቅና ለኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር በኪራይ የሚሰጠው ሥምምነት በሁለት ወራት ገደማ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለባሕር ኃይል የጦር ሠፈር ልትከራይ የምትችላቸው ሦስት አማራጭ ቦታዎች መለየታቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ዲፕሎማቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሙሴ ቢአብዲ የተፈራረሙት “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” በመጪዎቹ ወራት ወደ ተግባር ይሸጋገራል ብለው እየጠበቁ ነው።

የመግባቢያ ሥምምነቱ ከአራት ወራት በፊት ታህሳስ 22 ቀን 2016 ሲፈረም ድርድሩ በአንድ ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ አስታውቆ ነበር። የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ የመግባቢያ ሥምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን እና የቴክኒክ ኮሚቴዎች መታጨታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

“ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ነበር” ያሉት ዶክተር ኢሳ ካይድ በረመዳን የጾም ወር ወቅት ሒደቱ ቢቀዛቀዝም በመጪዎቹ ወራት ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ሥምምነቱን ወደ ተግባር የሚያሸጋግር የመጨረሻውን ሥምምነት ሊፈራረሙ እንደሚችሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

“ሁሉም ነገር ሁለቱ ቡድኖች በሥምምነቱ ላይ ለመደራደር ሲገናኙ ይወሰናል” ያሉት ዶክተር ኢሳ “የሕግ እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች አሉ። በመጪዎቹ ወራት ምን አልባትም በሁለት ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ሳዓድ አሊ ሽሬ ሥምምነቱ ተፈርሞ “ዕውቅና ስናገኝ በዓለም አቀፍ መድረክ ድምጽ ስለሚኖረን በፖለቲካ ረገድ ጠቃሚ ነው” ሲሉ ተስፋቸውን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።

ሶማሌላንድ የምታገኘው ዕውቅና “ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድ፣ ለጉዞ እና በዕድገት በር ስለሚከፍት በኤኮኖሚ ረገድ ጠቃሚ ይሆናል” የሚሉት የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሶማሌላንድ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት እንድትተሳሰር ይረዳታል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል።

“ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ መበደር እንችላለን” ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ሳዓድ አሊ “በዕውቅናው ምክንያት እጅግ በርካታ በሮች” ለሶማሌላንድ እንደሚከፈቱ ይጠብቃሉ።

ሥምምነቱ ከተፈረመ ሶማሌላንድ ዕውቅና ስታገኝ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር የምታቋቁምበትን ወደብ በኪራይ ታገኛለች። ሶማሌላንድ 850 ኪሎ ሜትር ገደማ በሚረዝመው የባሕር ዳርቻ ኢትዮጵያ ልትከራይ የምትችልባቸውን ሦስት ቦታዎች በአማራጭነት መለየታቸውን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ አረጋግጠዋል።

“የለየናቸው የተወሰኑ ቦታዎች አሉ። ከኢትዮጵያ አቻዎቻችን ጋር ከተገናኘን በኋላ አንዱ ይመረጣል” ያሉት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተለዩትን ሦስት ቦታዎች ስሞች ከመናገር ተቆጥበዋል።

ኢትዮጵያ የደርግ ሥርዓተ መንግሥት ወድቆ ኤርትራ ነጻነቷን ስታውጅ የፈረሰውን የባሕር ኃይል መልሳ ያቋቋመችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በፈረንሳይ እና የቀድሞ የባሕር ኃይል መኮንኖች ድጋፍ የባሕር ኃይሉን በአዋጅ መልሶ ያቋቋመው በ2011 ነበር።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
13.5K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 17:43:40 የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ!

የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት (ካውንስል) ኢትዮጵያውያን ላይ በጊዜያዊነት የቪዛ ገደብ ማሳለፉን አስታወቀ።በአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ድረ ገጽ ላይ ዛሬ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ. ም. በወጣው መግለጫ መሠረት፣ በአውሮፓ ኅብረት ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ ተደርጓል።

በዚህ ዕገዳ መሠረት፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም።ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉም።

የዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም።በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።መግለጫው እንደሚለው፣ ይህ ውሳኔ በኮሚሽኑ የተላለፈው “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ካውንስሉ ባደረገው ግምገማ ስለተገነዘበ” ነው።

አክሎም “የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዜጎችን መልሶ ለመውሰድ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም” በማለት መግለጫው ያብራራል።የአስቸኳይ ጊዜ የጉዞ ሰነዶች በመስጠት እንዲሁም በፍቃድ እና ያለ ፈቃድም የሚደረግ ስደተኞችን የመመለስ ሂደትን በተመለከተም ኢትዮጵያ “በቂ ትብብር አላደረገችም” ሲልም መግለጫው የውሳኔውን ምክንያት ያስረዳል።ስደተኞችን በመቀበል ረገድ በኢትዮጵያ በኩል ያለውን “ትብብር” በድጋሚ እንደሚቃኝም ኮሚሽኑ አክሏል።

በአውሮፓ ኅብረት የቪዛ ሕግ መሠረት፣ ኮሚሽኑ አገራት ስደተኞችን መልሶ በመቀበል ረገድ ያላቸውን ተባባሪነት እንደሚገመግም በድረ ገጹ የወጣው መግለጫ ይገልጻል።በኢትዮጵያ በኩል ስደተኞችን የመቀበል መጠኑ “አናሳ” እንደሆነ ጠቅሶ፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ለኢትዮጵያ ያቀረቡት ስደተኞችን የመመለስ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ “እምብዛም አለመሆኑ” ያለውን ትብብር “ትንሽ” ነው ብሎ እንዲደመድም ምክንያት እንደሆነው ማብራሪያ ሰጥቷል።ውሳኔው ጊዜያዊ ቢሆንም ቀነ ገደብ እንደሌለው የኮሚሽኑ መግለጫ ይጠቅሳል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
14.3K views14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 17:40:01
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ?

ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential
Customers) እንዲደርስስ?

-ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤
-በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤
-በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን።

ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ።

ቴሌግራም፡ @adsommar
ስልክ፡ 0954260423
13.1K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 15:07:47
በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል!

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል::ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
13.8K views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 12:19:45
50 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዉያን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ባለመሆናቸው በጨለማ ዉስጥን እንደሚገኙ የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ገልጿል!

ሚኒስትሩ እንዳለዉ በሀገሪቷ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት 50 በመቶ ማድረስ መቻሉንና ነገር ግን የተቀረው የማህበረሰብ ክፍል በጨለማ ዉስጥ እየኖሩ ይገኛሉ ብሏል።

በኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍ አደረጃጀቱን ለመቀየር ከዓለም ባንክ 552.6 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የገለፀው ሚኒስትሩ አሁን ላይ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት የማዘመን፣ ማደስ፣ ተጨማሪ የማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ማዕከላትን የመገንባት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

@YeneTube @FikerAssefa
14.1K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ