Get Mystery Box with random crypto!

ገበታ Recipes®

Logo of telegram channel gebeta_recipes — ገበታ Recipes®
Logo of telegram channel gebeta_recipes — ገበታ Recipes®
Channel address: @gebeta_recipes
Categories: Food
Language: English
Subscribers: 3.15K
Description from channel

Do you want to cook something different today ? Or do you want to give a spicy twist to your daily boring recipes? Then you are at right place .Enjoy our channel and learn the art of cooking foods and recipes.
Admin: [ @Tiletimothy @fasika_girma ]
አጣጥሙት

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


The latest Messages

2022-01-07 09:33:28
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ ፥ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

@Gebeta_Recipes
482 viewsedited  06:33
Open / Comment
2021-09-27 12:09:11
እንኳን ለመስቀል በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን፡፡
Happy Damara and Meskel Holiday.

@Gebeta_Recipes
634 views09:09
Open / Comment
2021-09-05 17:21:46 ፍራይድ ቺክን

• ግብዓቶች
• 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
• 2 የቡና ስኒ (100 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
• 5 የተመታ ዕንቁላል
• 1 ዶሮ (ከ800 ግራም እስከ 1 ኪሎ ግራም የሚመዝን)
• 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
• 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
• 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገባበት ቅቤ

• አሰራር
1. ዶሮውን መበለትና ማፅዳት፤
2. እያንዳንዱን ክፍል በሥጋ መቀጥቀጫ ጠፍጠፍ አድርጎ ማዘጋጀት፤
3. የፉርኖ ዱቄት፣ ጨውና ቁንዶበርበሬውን መቀላቀል፤
4. የዶሮውን ስጋ በተዘጋጀው ዱቄት መለወስ፤
5. እያንዳንዱን የተመታው እንቁላል ውስጥ እየነከሩ ወዲያውኑ በጋለ ዘይት መጥበስ ፤
6. ሥጋውን ትሪ ላይ መደርደር፤
7. ቅቤውን ቡናማ መልክ እስኪያወጣ አቅልጦ ላዩ ላይ ማፍሰስ።

@Gebeta_Recipes
1.3K views14:21
Open / Comment
2021-09-05 17:21:38
@Gebeta_Recipes
1.1K views14:21
Open / Comment
2021-08-22 17:19:45 ክሬፕ ሱዜት
Crepe suzette

• ግብዓቶች
• 2 ፍሬ ብርቱካን
• 2 መለኪያ የአናናስ አረቄ
• 4 ክሬፕ ቂጣ
• 4 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
• 4 የሻይ ማንኪያ ስኳር
• 2 ብርቱካን ጁስ
• አሰራር
1. የክሬፕ ቂጣውን በቅድሚያ ማዘጋጀት፤
2. ብርቱካኑን መጭመቅ፤
3. ሁለቱን ብርቱካን ልጦ እያንዳንዱን መፈልቀቅ፤
4. በፍልቃቂው ላይ ያሉትን ቆዳዎች መላጥ፤
5. በመጥበሻ ላይ ቅቤውን ማቅለጥ፤
6. የተፈለቀቀውን ብርቱካን መጨመርና ስኳር ከላዩ ላይ መነስነስ፤
7. የብርቱካን ጁሱን እና የአናናስ አረቄውን ጨምሮ አልኮሉ በደንብ እስኪቃጠል ድረስ ማብሰል፤
8. የተሰራውን ክሬፕ ከተሰራው የብርቱካን ሶስ ላይ ማድረግ፤
9. ትንሽ ከሞቀ በኋላ ክሬፑን አንሰቶ ሶሱን ከላይ መጨመር፤
10. ለሁለት ቆርጦ ማቅረብ።

@Gebeta_Recipes
283 views14:19
Open / Comment
2021-08-22 17:19:37
@Gebeta_Recipes
279 views14:19
Open / Comment
2021-08-11 17:34:08 የቱና ትራሜዚኒ
Tuna Tramezzini

• ግብዓቶች
• 2 የሻይ ማንኪያ ፐርስሊ
• 4 የሾርባ ማንኪያ ማዮኔዝ
• ሰላጣ
• 8 ስላይስ የተደረገ ዳቦ
• ጨውና ቁንዶበርበሬ
• 150 ግራም ቱና (2 ትንንሽ ቆርቆሮ የታሸገ ቱና)
• 2 ፍሬ ቲማቲም
• 1 ሎሚ ጭማቂውን
• አሰራር
1. ቱናውን ቆርቆሮውን ከፍቶ ዘይቱን ማጥለል፤
2. ቲማቲሙን አጥቦ በደቃቁ መክተፍ፤
3. ቱናውን ጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ አድርጎ ቲማቲሙን መጨመር፤
4. ፐርስሊውን በደቃቁ ከትፎ መጨመር፤
5. ሎሚ፣ ማዮኔዝ፣ ጨውና ቁንዶበርበሬ አድርጎ ሁሉንም በደንብ ማደባለቅ፤
6. ሁለት ስላይስ ዳቦ አዘጋጅቶ በሁለቱም በኩል ማዮኔዝ መቀባት፤
7. የተቀላቀለውን ቱና በዳቦው በአንድ በኩል ላይ አስቀምጦ ቱናውን ማዳረስ፤
8. ሁለተኛውን የዳቦ ስላይስ ቱና የያዘው ስላይስ ላይ መደረብ፤
9. ሁሉም ሳንድዊች ተሰርቶ ካለቀ በኋላ እስከሚበላ ድረስ ዳቦው እንዳይደርቅ በጥቂቱ ረጠብ ያለ የኪችን ፎጣ ሸፍኖ ማስቀመጡ ይመረጣል።

@Gebeta_Recipes
607 views14:34
Open / Comment
2021-08-11 17:33:23
@Gebeta_Recipes
597 views14:33
Open / Comment
2021-08-05 19:09:26 Guacamole
ጉዋካሞሊ

• ግብዓቶች
• ግማሽ ራስ ቀይ ሽንኩርት
• ጨውና ቁንዶበርበሬ
• 2 ፍሬ አቮካዶ
• 1 ፍሬ ቲማቲም

• አሰራር
1. አቮካዶውን ልጦ ለሁለት ቆርጦ በደቃቁ መክተፍ
2. ሎሚውን ቆርጦ ጁሱን ማውጣት፤
3. የወጣውን የሎሚ ጁስ ወደ አቮካዶው ውስጥ መጨመር፤
4. ቲማቲሙን አጥቦ በትናንሹ መክተፍ፤
5. ሽንኩርቱን በደቃቁ መክተፍ ፤
6. ቲማቲምና ሽንኩርቱን አቮካዶውን ውስጥ መጨመር፤
7. አስፈላጊ ከሆነ አንድ ቃሪያ በደቃቁ ከትፎ አቮካዶው ውስጥ መጨመር፤
8. ጨውና ቁንዶበርበሬ ጨምሮ ከዳቦ ወይም ከቂጣ ወይም ከችፕስ ጋር ማቅረብ።

@Gebeta_Recipes
475 views16:09
Open / Comment