🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሰበር ዜና አሜሪካ ከሩሲያ እንዲዋጋ ወደ ዩክሬን የምትልከው ጦር እንደማይኖር አስታወቀች በሩሲያ | Merega Tv = Ethio 360Media

ሰበር ዜና

አሜሪካ ከሩሲያ እንዲዋጋ ወደ ዩክሬን የምትልከው ጦር እንደማይኖር አስታወቀች በሩሲያ አራት ባንኮች ላይ ከባድ ያሉትን እገዳ መጣላቸውንም ነው ባይደን ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት

ለዩክሬን በአንድ ዓመት ብቻ የ650 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ወታደራዊ ድጋፍ አድርገናል ያሉት ፕሬዝዳንት ባይደን ወደ ዩክሬን የምንልከው ጦር የለም ብለዋል

አሜሪካ ለውጊያ ወደ ዩክሬን የምትልከው ወታደር እንደማይኖር ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ።

ባይደን ሩሲያ አቅዳ የፈጸመችው ነው ያሉትን የዩክሬን "ወረራ" በተመለከተ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው እንወስደዋለን ካሉት የማዕቀብ እርምጃ ጋር የተያያዙ ማብራሪያዎችንም ሰጥተዋል።

ፑቲን ወራሪ ነው፤ ጦርነትንም መርጧል" ሲሉ" በማብራሪያቸው የሩሲያን ፕሬዝዳንት የወነጀሉት ባይደን አሁን ገፈቱን መቅመስ ይጀምራል ሲሉ ተናግረዋል።

ወደ ሩሲያ ኤክስፖርት በሚደረጉ ምርቶች ላይ ከበድ ያለ ማዕቀብ መጣላቸውን ያስታወቁም ሲሆን ማዕቀቡ የሩሲያን ምጣኔ ሃብት በአጭርና በረጅም ጊዜ እንደሚያንኮታኩተው ገልፀዋል።

ሆኖም ይህ አሜሪካ በተናጠል ሳይሆን 27 የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራትን ጨምሮ ከዓለም ምጣኔ ሃብት እኩሌታውን ከያዙ አጋሮቿ ጋር የምታደርገው ነው ብለዋል።

ዛሬ ጠዋት (ሃሙስ) ከቡድን 7 አባል ሃገራት ጋር በነበረ ስብሰባ በዚሁ ጉዳይ ላይ መስማማታቸውን የገለፁም ሲሆን ሩሲያ በዶላር፣ በዩሮ ፣ በእንግሊዝ ፓውንድ እና በጃፓን የን መገበያየቷን እንገድበዋለንም ብለዋል ፕሬዝዳንት ባይደን።

በአሜሪካ በሚንቀሳቀሱ እና በጥቅሉ ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ለማካበት የቻሉ አራት የሩሲያ ባንኮች ሃብታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ እገዳ መጣሉንም ገልጸዋል።

ለፕሬዝዳንት ፑቲን ቅርበት ባላቸው አካላት የንግድ ተቋማት እና ሩሲያ ከአሜሪካ በምታስገባቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ማዕቀብ መጣሉንም ነው ይህ ወታደራዊ ብርታቷን ክፉኛ ያዳክመዋል ያሉት ባይደን ያስታወቁት።

ሆኖም የአሜሪካ ጦር ወደ ዩክሬን አቅንተው በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት እንደማይሳተፍ አልሸሸጉም።

"ወታደሮቻችን በዩክሬን ውጊያ ለመሳተፍ ወደ አውሮፓ አይሄዱም" ሲሉም ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት፤ ሃገራቸው ለዩክሬን የ650 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጓን በመጠቆም።

ይልቁንም ጦሩ የኔቶ (የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት) አባል የሆኑ የምስራቅ አውሮፓ አጋር ሃገራትን ለመጠበቅ ወደዚያው እንደሚያቀና ባይደን ተናግረዋል።

ኔቶ ለአጋሮቹ ዋስትና መስጠት በሚችልበት ጉዳይ ላይ ለመምከር ነገ አርብ አስቸኳይ ስብሰባን እንደሚያደርግም አያይዘው ገልጸዋል።

አሜሪካ ሙሉ በኔቶ ቁጥጥር ስር ያለችን እያንዳንዷን ይዞታ ኢንች እንኳን ሳታስቀር ትጠብቃለችም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።