Get Mystery Box with random crypto!

★★ ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ★★ ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ ቀልደሽ ተጫውተሽ ስቀሽ እያሳቅሽኝ ሳታው | መፅሐፍት

★★ ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ★★


ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ
ቀልደሽ ተጫውተሽ ስቀሽ እያሳቅሽኝ
ሳታውቂው ሄደሻል ፍቅር አሲዘሽኝ
ለካ አንቺ ልብሽን አሳምነሽዋል
ንፁህ ወንድሜ ነው ብለሽ ነግረሽዋል
አልሰማ አለኝሳ የኔን ልብ ብነግረው
አንቺን እንደ እህትህ ውደድልኝ ብለው
ልቤን ብጠይቀው አጫወተኝ ብዙ
በመውደድ መስከሩን በፍቅርሽ መያዙ
ከዚያን ቀን ጀምሮ
ውስጤ ይፈራ ጀመር አንቺን ሲያይ አይኔ
ልቤ ሲሄድ ታየኝ ተለይቶኝ ከኔጠየቁኝ ጓዶቼ
የኔ እንደዚ መሆን ግራ ቢገባቸው
የት እንሂድ ሲሉ አንቺ ጋር
ስላቸው
ስለወደድኳት ነው ብዬ ነገርኳቸው
ስቀውብኝ ነበር ምቀልድ መስሏቸው
ጨዋታዬ ጠፍቶ በዝቶ መጨነቄ
ሲገባቸው ዛሬ በፍቅርሽ,, መውደቄ
ንገራት እያሉኝ እያለፍኩኝ ስቄዘገየሁ
መሄጃሽ ደረሰ ካይኖቼ ልትርቂ
ስታወሪ ላልሰማ ላላይሽ ስትስቂ
ሳልነግርሽ ማፍቀሬን ዛሬ ነገ እያልኩኝ
ሄደሽብኝ አዘንኩ በሀሳብ ባከንኩኝ
ጨዋታሽ ሳይበቃኝ ሳልጠግብሽ አይቼ
ማፍቀሬ ሳይገባሽ ሳልነግርሽ ፈርቼ
መውደዴን ማስረጃ አንደበት አጥቼ
አዘንኩኝ በራሴ ሄደች ያሉኝ ለታ
ጨለመብኝ በቃ ቀኑም እንደማታ
አስጠላኝ ሰፈሩ አንቺ የሌለሽበት
ልቤ ሀዘን ገባው ሄደሽ ቀርተሽበት
ልነግርሽ ወስኜ
ጠይቄ ጓዶቼን ምን ልበላት ብዬ
ብነግርሽ ደፍሬ ፍራቻን ገድዬ
መውደዴን ጠላሽው ማፍቀሬን ገፋሽው
ለስንት የታሰበው በአጭር ቋጨሽው
እኔኮ ሆዴ
አልጠላም ነበረ ባይሽ እንደ እህቴ
ሳላስበው ገብተሽ ባትበይው አንጀቴ
አንቺን መርሳት አልቻልኩ አቃተኝ ሞክሬ
ከሀሳቤ አትጠፊም ትላንት ሲያልፍ ዛሬ
በሀሳብ አይሻለሁ ላይኔ ስትርቂብኝ
ትዝታሽን ብቻ ጥለሽ ሄደሽብኝ
ተጎዳሁኝ ውዴ አንቺን ስል ቀን ማታ
በአካል ነይልኝ በትዝታሽ ፈንታ ፣ ።

@BarkoteA