Get Mystery Box with random crypto!

ያልተስተዋለ እውነት በሁሉ ንግስ እለት የኔ ቢጤ ወድቆ ወጣቱ ሲዘምር ሰዉ ይገረማል አዛውንት | መፅሐፍት

ያልተስተዋለ እውነት

በሁሉ ንግስ እለት
የኔ ቢጤ ወድቆ ወጣቱ ሲዘምር ሰዉ ይገረማል
አዛውንት ጠውልገው ካህኑም ወዝ ሲይዝ ያኔ ደርሶ ያዝናል
ሰው ብዙ አስተውሎ ብዙ ይናገራል

እኔ ግን እላለው
ሁሉ ምስጢር አለው

አዳፋ ልብስ አርጎ ለማኙ ቢበዛ የተደረደረው
ማፅደቂያ እንዲሆኑ ተብሎ ነው እንጂ
ፈጣሪ አቶ አይደል ለነሱ ሚሰጠው
ደግሞም በዚያ መሐል አምላክ እንዲህ ነበር ለኛ የተዋረደው
በዚያች ክፉ አለም እንዲያ ሞቼ ነበር
አሁን ግን ተነሳው እልል ይበል ምድር
ይላል በወጣቱ ዝማሬ ላይ አድሮ
የሚያገለግለኝስ መቼ ይቀራል ወድቆ
ሲል አምላክ ይታያል
የካህናቱን ፊት በወዝ ቀለም ስሎ
ከቤተ ክርስቲያኑ ውጭው እና ውስጡ
አንድ አለመሆናቸው መቼ የገባው ኑሮ
ከአውደ ምህረቱ ምስጢር ቢገለጥም
የሰው አይን ክፉ ነው
የአለም ገንዘብ እንጂ እውነት አያሳይም

ታድያ ይህ ያልገባው የዘመኑ ኗሪ
አምላክ ሊያዳላ ነው ብሎ ተናጋሪ
አይኑ በእውነት አስተዋልኩኝ ካለ
ለወቀሳ ሩጦ ምስጢር ካልተማረ
ጥያቄዬ ይሄ ነው
ለሱ ያልታየው እውነት ለምን ለኔ ታየ?

@MyMessagesss