Get Mystery Box with random crypto!

ቀን ሳለህ ተማፀን ደስተኛ ይመስላል ፤ ሁሉ የሞላለት ማን በነገረው፤ መልክ ብቻ እንዶነ ፣ነጠ | መፅሐፍት

ቀን ሳለህ ተማፀን

ደስተኛ ይመስላል ፤ ሁሉ የሞላለት
ማን በነገረው፤ መልክ ብቻ እንዶነ ፣ነጠለ ና ጥለት

ውስጤን ፅልመት ሞልቶት፣ ዘውትር እየቀጣኝ
በአምላክ ፊት ማስመሰል፣ ምክንያቱ እየጠፋኝ
አልቅስ አልቅስ ሲለኝ፣ ነፍሴን አየከፋው
የፅልመት ንጉሡን፣ ውሸት እየሰማሁ

ደህይቶ መኮፈስ
የሚበሉት አቶ፣ በልተው እንዳደሩ፣ ለፊት መንፈላሰስ
ለምን ሆነ ህይወቴ? ፣ ለምን ሆነ እውነቴ?
ለምኖ ለመብላት፣ እራሱን ለማዳን፣ ለምን ፈራ ፊቴ?

በሰው ፊትስ እሺ፣ ይሁን ልሳቅ ለይምሰል
ፅልመቴን ከሚያውቀው ከመድሃኔ ዓለም ፊት፣ ለምንድን ላስመስል?
ተው ግን ይሻልሀል፣ ህይወቴ አንባ አልቅስ
ለይምሰል እየኖርክ፣ የእውነት እዳትሞት፣ በአምላክ ፊት እንዳትረክስ
ነገ ነገ እያልክ፣ የሞት ዛሬ መቶ፣ ነጥቆ ይወስድሃል
ያኔ ከመቃብር ፣ የይምሰል ህይወትክ፣ ሚያድንህ ይመስልሃል?
ዓይንህ ከመሬት ስር፣ ገብታ አታለቅስልህ
እግርህ አመድ ሆኖ፣ ላንተ አይሰግድልህ

እባክህን ስማኝ
ቀን እያለህ አዘን፣ ቀን ሳለህ ተማፀን
ሁሉ ያበቃ እለት፣ ሙሉ እንድትሰኝ
ቀን እያለህ እዘን፣ ቀን ሳለህ ተማፀን።

@MyMessagesss