Get Mystery Box with random crypto!

የልቤ አጥሩን አፍርሰህ የገባህ ደረቅ እኔነቴን በፍቅር የገነባህ አንተ ማነህና....... እኔ | መፅሐፍት

የልቤ አጥሩን አፍርሰህ የገባህ
ደረቅ እኔነቴን በፍቅር የገነባህ

አንተ ማነህና.......

እኔ ሳዋርድህ አክብረህ ምጠራኝ
ስገፋህ እያየህ አቅፈህ የምትስመኝ።

ምን ይለይህና......

ስወድህ ሳትሸሸኝ ፍቅርህ የማይቀንስ
ስቀርብህ ሰልችቶህ ቃልን የማታፈርስ።

ማነህ አንተ ኩሩ
የ'ዳም ዘር ማንዘሩ
የግዜር የቃል ግብሩ
ስበድል እንኳ አይተህ የማታልፍ ከበሩ።

እኔስ ማነኝና...........

ባንተ ማልሸነፍ
በፍቅርህ የማልከንፍ
በመዉደድ የማልቀዝፍ
የልጆቼን ታሪክ ባንተ እቅፍ የማልፅፍ።

እኔ ማነኝና.............
እምምምምም
በቃ እንጋባ


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ


@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@audio_poems
@audio_poems