Get Mystery Box with random crypto!

አንቺ ፧ ፧ ( ዮሐንስ ሀብተማሪያም ) ፧ ፧ ደህናይቱ!!! መልካሚቱ!!! አንቺ!!! የጅምሬ | መፅሐፍት

አንቺ


( ዮሐንስ ሀብተማሪያም )


ደህናይቱ!!!
መልካሚቱ!!!

አንቺ!!!

የጅምሬ መሰረቱ፡፡

የቀኝ መዋያ ልኬቱ
የደግ እጣዬ ድምቀቱ፡፡

የቀልብያዬ ስሪቱ
መንፈላሰሻ ምቾቱ፡፡

መታመኛዬ መቅደሴ
ሕያው መኖሪያ ለነፍሴ፡፡

ቅኔ ማኅሌት ለያሬድ
ታላቅ ቅዳሴ ለኤፍሬም

ፅና መስቀሉ ለአማኝ
እጣን ከርቤው ነሽ ለዓለም፡፡

እስከዘላለም ዘላም
ለዘለዓለም አሜኑ

የሩሔ ረቂቅ ስምረቱ
ነግሶ ፃድቅም መሆኑ፡፡

ደህናይቱ!!!
መልካሚቱ!!!

አንቺዪቱ!!!!

የቀን ሰመመን ስፍሬ
መፈላሰፊያ ቀመሬ።

በሐቁ ወገን መኖሬ
በቅኑ መጠጥ ስካሬ፡፡

የኔ እኔነት ፍካሬ
ሁላ ሁሉዬ ለፍቅሬ
ዘላለማዊ መስመሬ፡፡

አንቺ!!!

ሰማያዊ ዳስ ላ'ብርሐም
የመስተንግዶው ማሕተም፡፡

ከምድር ሰማይ መሰላል
የቃል ኪዳኔ ልዪ ቃል፡፡

እንደርግብ ላባ ለስላሳ
የዋህነትሽ ግሪሳ፡፡

ያንበሳ ጉፈር ግርማዊት
ዥንጉርጉር ቀለም ነብራዊት
የማትለ'ቂ ኢትዮጵያዊት፡፡

አንቺ!!!

ምሬታዊነት መጣፈጥ
በተነኪነት መመሰጥ
ሐቂቃ ኩነት ለመግለጥ፡፡

እኔን ያተጋሽ መሰጠት
ቅኔን የቃኘሽ መለኮት
የመነካቴ አብነት፡፡

ወደመጡበት ለመምጣት
የሄዱበትን ለመሄድ

በሕይወት እውነት መወለድ
ከእውነት ሕይወት መናገድ፡፡

አንቺ!!!
አንቺ!!!

አንቺ ብቻ አንቺ!!!

ምስጢር የምትፈቺ
እኔን የምትረቺ፡፡


https://t.me/MyMessagesss