Get Mystery Box with random crypto!

'መሰከረም' ላይ . . በጋ ሲሆን ገና፤ አውልቆ ለመጣል የወበቁን ድባት፣ ነፍሴን ለማለምለም ፍቅር | መፅሐፍት

"መሰከረም" ላይ
.
.
በጋ ሲሆን ገና፤
አውልቆ ለመጣል የወበቁን ድባት፣
ነፍሴን ለማለምለም ፍቅር ለመጋራት፣
ቃል እየወለድኩኝ፤
ቀን እየማለድኩኝ፤
ፍቅሬን "ነይ" አልልም፡፡
ለሙቀት ሳልሰጋ፤
ወረተኛው በጋ፤
እኔን ሳያማክር እንደመጣ ያልፋል፣
ክረምት አስከትሎ ከፊት ይሰለፋል፡፡
.
.
ቁር እየወለደ፤
ብርዱ ሲደራረብ በክረምቱ ወራት፣
ፍቅር ብትጠማ ነፍሴን ሰው ቢርባት፡፡
ውርጩን ስረፈራሁ ጣፋጯን በማለም፣
ቃል እያሰማመርኩ ፍቅሬን "ነይ" አልልም፡፡

በወፍ ጎጆዬ ውስጥ፤
በወፍራም ሹራብ ላይ ካቦርቴን ደርቤ፣
ቦት ተጫምቼ፤
ጋቢ ወይ ብልኮ አንዱን ተከንቤ፡፡
ሸንቁር ምድጃ ላይ፤
እሳት አያይዤ እሸት እየጠበስኩ፣
ውርጩን እያሟሸሁ ብርዱን እየሰበርኩ፣
~ክረምቴን አልፋለው፣
ለሊት በህልም አክናፍ፤
ካንዱ ምዕዋር ላይ ሙቀት እቀዝፋለዉ፡፡

ይልቅ፤
በዘመን ማለዳ፤
በፀደይ ተወልዳ፤
ደመናው ተንዶ ጀምበሯ ስትወጣ፣
እንደ መልካም እድል፤
እንደ መስቀሏ ወፍ ባ'ደይ ተንቆጥቁጣ፣
ያምላኬ ስጦታ፤
የምወዳት ፍቅሬ "መስከረም" ላይ ትምጣ፡፡

ትምጣ ትዝታዬ፤
ታሽረኝ ከመድከም፤
ዝለቴን ታክመው ተሽጣ ከጎኔ፤
የናፈቁት ገላ "እቅፍ" ሲያረጉት ፋሲካ ነው ያኔ፡፡

ዐብይ


https://t.me/MyMessagesss