Get Mystery Box with random crypto!

ምናብ ትመስይኛለሽ እንደ የቀን ህልሜ እንደ ደራሽ ፀሎት፣ ፅናቴን ፈትና እንደረካች እምነት። | መፅሐፍት

ምናብ ትመስይኛለሽ
እንደ የቀን ህልሜ
እንደ ደራሽ ፀሎት፣
ፅናቴን ፈትና
እንደረካች እምነት።

ደሞ ስንለወጥ
ጊዜ ሲያይልብን፣
በወጀብ መሀከል
ስንቃዥ ለነብሳችን፣
ምናብ ይመስለኛል
የኖርነው ፍቅራችን
ስሜ 'ሚናፍቀኝ
እንቡጥ ከንፈርሽን፤

ግን አለሁ፥
ዛሬም  እንደተከዝኩኝ
ምናብሽን እንዳደንኩኝ
(ግን አለሁ)
ትዝታሽን ተደግፌ
ከህይወትሽ ተሸርፌ
ናፍቆትሽን ለዕቅፌ
(ግን አለሁ)
ፈገግታሽን ተንተርሼ
መዓዛሽን ተፈውሼ
(ግን አለሁ)
ያች ቦታ ስጠብቅሽ
ምናብ ይመስለኛል
የሰማሁት ድምፅሽ።

https://t.me/MyMessagesss