Get Mystery Box with random crypto!

በርግጥ በኔ ዘመን .................... እምነት እንደ ጉሊት ሲቸበቸብ ያድራል ቃል አ | መፅሐፍት

በርግጥ በኔ ዘመን ....................

እምነት እንደ ጉሊት ሲቸበቸብ ያድራል
ቃል አክባሪ ግትር ተብሎ ይወቀሳል::

እዎ በኔ ዘመን......................

ፍቅር ከጭን ዳሌ ውሉን ያሳሰረ
የገበያው ዘዴ ሳይለዩ መግዛትን ብሂል የሰበረ::

በፍቅር ቅኝት ስም ሴሰኝነት ነግሶ
የነፍስ ፍቃዷ ተድሶ

በየ ጥጋ ጥጉ አስክሮ ሚያዳራ
ሺህ ጭኖችን ታቅፎ ሺህ ነፍስ የሚያሳጣ
የዘመናት ዋጋ.......
ወጣትነት ልኩ.........

መዝናናት ታቅፎ ውስጡ እዥ ያዘለ
በፈረሰ ደስታ ጠማማ ምሰሶ ታቅፎ የዋለ::

የእድሜ ጣሪያ ልስን
በእኔ ከሞትኩ ሰርዶ
በሺ አይኖር ወርዶ
በውሽት ቅብ ውበት ከላይ የተዋበ
አራዳ የሚያስብል አንዳንድ ስግጥና እለ::

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems