Get Mystery Box with random crypto!

'ለካስ ያን ዕለታ' አለም በቃኝ ብዬ ስኤድ ወደ አንድዬ ደረቱ ሲደለቅ ሁሉም ተሰብስቦ እሪታ | መፅሐፍት

"ለካስ ያን ዕለታ"

አለም በቃኝ ብዬ
ስኤድ ወደ አንድዬ
ደረቱ ሲደለቅ
ሁሉም ተሰብስቦ
እሪታውን ሲለቅ
ቅኔው ሲቀኝልኝ
ሞሾዎውም ሲወረድ
መሬቱ ሲመታ
እናት በአዘን ስትነድ
ወዳጅ ጎረቤቱ
ለኔ ልቡ ሲርድ
እግዜር ያፅናቹ
ሲል ሁሉም ተሰብስቦ
አስክሬኔ ሲሸኝ
በዘመድ ታጅቦ
የቤቴ ይቅርና
እንኳን የመንደሬ
የውል ስሜ ቀርቶ
ሲኬድ ለቀብሬ
እማዬ እምዬ
አባት አባት አለም
እህት የናት ምትክ
ወንድም የኔ ጋሻ
ዘመድ አዝማዶቼም
የጭንቄ መሸሻ
የለካስ ያንህለታ
ሞት አሸንፎት
ገላዬ ሲረታ
ክፋት ደግነቴን
ሊዘረዝልኝ ሁሉም ሲበረታ
ለካ ያን ለታ
ሁሉም ይረሳና
ስሜ ይቀየርና
እሬሳ እባላለሁ
በድን ሰው ነኝና


https://t.me/MyMessagesss



https://t.me/MyMessagesss




https://t.me/MyMessagesss