Get Mystery Box with random crypto!

ፍርክስክስ በሬን ከረቸምኩኝ             ጠረቀምኩኝ መስኮት፤ ከቤቴ ይሰርጋል ያንቺ ነገር | መፅሐፍት

ፍርክስክስ

በሬን ከረቸምኩኝ
            ጠረቀምኩኝ መስኮት፤
ከቤቴ ይሰርጋል
ያንቺ ነገር ምትሀት ልክ እንደ መለኮት...

ይመጣል እንደ ጭስ
መች መግቢያውን ያጣል፤
አፍን ቢከድኑበት
ቲሊሊል እያለ በአፍንጫ ይዘልቃል፤
አለው መሰለኝ ቃል. . .

መች መግቢያውን ያጣል

በጆሮ በዓይኔም ከውስጠቴ ዘልቆ፤
መልሶ ይቆጣና
ያ ኮስማና ልቤን የተወሽን ንቆ...
ባንቺነትሽ አመል
ብጥስ ያለ አንጀቴን ይጠጋግንና፤
እህ.... በቃኝ ያለ
የቆረጠ ሆዴን "ገር ሁን" ይለውና...
መደቡን ይሰራል
ቆጥ ከላይ ያበጃል ደግሞ ሊደላደል፤
እንዲህ እንደዋዛ
መች ርቆ ይሄዳል
ካልሞትኩለት በቀር....

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1