Get Mystery Box with random crypto!

ስንት ጊዜ ይፈጃል ምን ያህል አመታት ስንት ሰዉ ይበቃል ትዝታን ለመርሳት ምን የሚሉት ጂኒ ካንተ | ግጥም በድምፅ

ስንት ጊዜ ይፈጃል ምን ያህል አመታት
ስንት ሰዉ ይበቃል ትዝታን ለመርሳት

ምን የሚሉት ጂኒ ካንተ ጋር አሰረኝ
የትኛዉ መለኮት በፍቅርህ ጠፈረኝ

በየትኛዉ ጥበብ በየትኛዉ ዘዴ
በየትኛዉ ብልሀት አወከዉ የሆዴን

እንጃ................
ጊዜም መልሱ ጠፋበት መሰለኝ
ካንተ ጋር ይነጉዳል ጥያቄ እያጫረኝ

ስንት ዘመን ቀረኝ
ስንት እድሜ ይተርፈኝ
መቼ ያሳርፈኝ

ትዝታህ ጠቢቡ
ትዝታህ ብልሁ

ትዝታህ ብልጥ ወዳጅ
እያሳሳቀ ነዉ አብሮ ሚያሳቅቀኝ
እያጫወተ ነዉ እድሜዬን የቀጨኝ

ወይ እሱ ይተወኝ ወይ አንተ ደግመህ ና
ትዝታህን ዉሰድ እኔን መልስና።
.........................
.........................

ትዝታ ወልዴ

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems