🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ደህና ነበርኩ እኮ ሳልወድሽ በፊት ገና ልቤ ሳትነግሽ በአይኔ ሳትዞሪ እንደውሃ ሳትፈሽ እንደልጅ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ደህና ነበርኩ እኮ

ሳልወድሽ በፊት ገና ልቤ ሳትነግሽ
በአይኔ ሳትዞሪ እንደውሃ ሳትፈሽ

እንደልጅ ጨርቅ ኳስ አይኔ ሲንከባለል፣
ያላወቀ መስሎ በአንቺው ሳይደለል

መርሳት ራሱ ራሴን ሳይረሳው
የሸጥኩት ደስታዬ በውድ ሳለምነው

ፊቴ ወዝ ሳያጣ ትዝታን ሳይተካ
ዓይኔ ሳያብጥ የእንባ ውሃ ሳይነካ

ፀጉሬ ሳይጨበርር ቅባት ሳያጣው
ከንፈሬ ሳይደርቅ መሳምሽ ሳይመታው
አይኔ ውሃ ሳያጣ ትዝታሽ ሳይሞላው
የአሁን መልኬን ጎረቤት ሳይጠላው

ያኔ ገና ሳልወድሽ በነበርኩ
ማሪያምን ነው ምልሽ እኔ ደና ነበርኩ


ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19