🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ከደበረህ አይቀር እንካ ከኒንህን እስከፈለክ ዋጠው ዶዙ ካናት ይውጣ              ልብህን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከደበረህ አይቀር
እንካ ከኒንህን እስከፈለክ ዋጠው
ዶዙ ካናት ይውጣ
             ልብህን ያናውጠው
ገደል ትግባ ፀሃይ
              ጨረቃም እንደዛው
ዛሬ የዋጥከውን ለነገ አባዛው
ሁሉም ውሸት ብቻ
           ድርሰትና ግጥም
ለራስ መና ናቸው
           ውስጥህን አጣጥም
ከፈለክ ጠጣበት
            እንዳሻህ ተንቦራጭ
ተታግለህ አሸንፍ
            እንደ ርቀት ሯጭ

ስማቸው......

አየህ....

የሚያነቁ አንደበት ቢሰራጭ በአለም
        ገፋ አርገህ ተዋቸው
ህይወት መቀየሪያ
               ብር ይስጡህ ካሻቸው

ግን

እስክትወጣ ድረስ የግልህ ጨረቃ
በትዝብት ዝም በል ትተሃቸው ንቃ
ተደበቅ ከአለም ከራስህ ጋር አውጋ
እስኪፈካ ድረስ የግልህ ብርሃን
        ፀሃይ እስክትነጋ
ውድቀትን አጣጥም
በውድቀት ነውና ስኬትህ የሚጥም

ከደበረህ አይቀር...ይኸው መድሃኒትህ
      እስከፈለክ ዋጠው
ውስጥህ እርብሽ ይበል
              ልብህን አናውጠው
ገደል ትግባ ፀሃይ ላንተ ካላበራች
ሺህ ቀን ጠፍታ ትክረም ብርሃንህን ካጣች

ይኸው ያዝና ዋጥ!

ህመምን ያወቀ ውድቀትን አይፈራም!

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19