Get Mystery Box with random crypto!

መልከ ቀና አድርገኝ ህይወቴ ቢቀለኝ.. . አውለኝ በክብር ቀባኝ ሞገስ ቅባት ቀኖቼ ላይ ልንገስ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

መልከ ቀና አድርገኝ
ህይወቴ ቢቀለኝ.. .
አውለኝ በክብር
ቀባኝ ሞገስ ቅባት
ቀኖቼ ላይ ልንገስ
በሌሎች ፍርሀት።
ስጠኝ የመሪ ድምፅ
አጥር የሚሻገር...
መንገዴ እንዲሳለጥ
እንዲሆን ገር በገር ።
አልያ አልገፋትም...
ይህችን ስንኩል ዕድሜ
ለአይን አስቀይሜ፥
ቀልዬ ያለ ሞገስ...
ሰው ሰሚ ሲያጣ ነው
ከሞት ደጅ የሚደርስ !!

(ሚካኤል.አ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19