Get Mystery Box with random crypto!

#እምቢ_ባይ_ልሳን የአመታት ስቃዬን አብሮኝ የኖረውን የሚረዳኝ ጠፍቶ መፍትሄ ያጣውን ጨክኜ ብነግ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#እምቢ_ባይ_ልሳን

የአመታት ስቃዬን አብሮኝ የኖረውን
የሚረዳኝ ጠፍቶ መፍትሄ ያጣውን
ጨክኜ ብነግራት ድብቁ ስሜቴን
በአንዲት ቁንፁል ቃል ናደችው ህይወቴን
እወድሻለሁ ብዬ ቃላት ሳዥጎደጉድ
አልወድህም ብላ አደረገችኝ ጉድ
:
ሂድልኝ ከዚህ ጥፋ ከፊቴ
ላይህ አልሻም አትድረስ ቤቴ
ብላ በዚች ቃል ክምሩ ፍቅሬን
አጠለሸችው ናደችው ክብሬን
የትኛው በደሌ የትኛው ጥፋቴ
ያለ ፍርደ ሸንጎ እንዲህ መቀጣቴ
:
እንዲያውም ልንገርሽ
ፍትህ አልባ ሰው ነሽ
.
በጠጣሩ ቃልሽ መጎዳት ባልሻም
እቀበለዋለሁ እውነቱን አልሸሽም
ምን ይደረጋል አንዴ ፈርደሻል
በኔ ከባድ ህመም መወሰን ቀሎሻል
:
አይባልም እንጂ.......
ስቃዬ ደርሶብሽ በራስሽ ፍረጂ
የሚረዳሽ ጠፍቶ በናፍቆት ንደጂ
ግን ይሁን እንደፈለግሽ...
ባፈቀረ ልቤ መልሼ አልርገምሽ
.
ካልወደድሺኝ አታስቢ
እንድትወጂኝ ብዬ እኔ አልወደድኩሽም
ጠልተሽኛል ብዬ ፍፁም አልረሳሽም
ግን እስከዚያው.....
ደንዳናው ልብሽን ፍቅር እስኪገዛው
እኔም የልቤን ወላፈን አፍኜ ልያዘው
.
ግን ግን እንዳትረሺ...
ትዝ ባልኩሽ ቁጥር ይህንን አስታውሺ
ይህ ደብዛዛ ፍቅሬ አንድ ቀን ከገባሽ
በልቤ ሰገነት ሁልጊዜም ቦታ አለሽ
ዛሬም ትላንትና ነገም ትኖሪያለሽ
{MU_EID}


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19