🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ናፍቆት ይሉትን ወግ ነፍስ እየሸመኑ ስጋ ካለበሱት ሸማኔዋን አንቺን ነጠላውን እኔን ነበር ሚያስመ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ናፍቆት ይሉትን ወግ
ነፍስ እየሸመኑ ስጋ ካለበሱት
ሸማኔዋን አንቺን
ነጠላውን እኔን ነበር ሚያስመስሉት

ባገሩ ሰው ሞልቶ የሚወርድ 'ሚወጣ
አልታይህ አለኝ
አንቺ ሸፍነሽው የመውደዴን እጣ

ትዝታ ብቻውን ናፍቆት ላያስወጣ ህመም ላያክመኝ
እየመላለሰ አንቺን አንቺን ብሎ ልቤን አደከመኝ

ትዝታ ውበቱ
የናፈቅሽኝ ለታ ትናንትን ማየቱ
ትዝታ ክፋቱ
የናፈቅሽኝ ለታ አሁንን መሳቱ


         በአቤኒ የተጻፈ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19