Get Mystery Box with random crypto!

ትናንት ባህል ሚነስትር የሚሰራ ሰው ደውሎልኝ “የልደት ቀንህን በማስመልከት የግልና የመንግስት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ትናንት ባህል ሚነስትር የሚሰራ ሰው ደውሎልኝ “የልደት ቀንህን በማስመልከት የግልና የመንግስት መስርያ ቤቶች ዝግ እንዲሆኑ ትፈልጋለህ ወይ?” ሲል ጠየቀኝ፤ መስርያቤቶችን ከፍታችሁ የአመት ወጭየን ብትዘጉልኝ ደስ ይለኛል “ የሚል ምላሽ ሰጠሁ፤ሰውየው ውጭየን በመዝጋት ፋንታ ስልኩን ጆሮየ ላይ ዘጋው :
ለማንኛውም፤ ከትክትክ ፥ ከተባራሪ ጥይት፥ ከሎንቺና ጎማ፥ ከኮረና፥ ከኮሌስተሮልና ከመሳሰሉት የችኩል ሞት መልክተኞች ተርፈን እዚህ ደርሰናል! በመወለዴ በመኖሬም ተደስታችሁ እንኩዋን ተወለድህ ያላችሁኝ እህት ወንድሞቼ እንዳከበራችሁኝ ያክብርልኝ፤

ኔትወርክ፥ ባለስልጣን ጥሎ እንደረሳው የመሰረት ድንጋይ ባያደናቅፈኝ ፥ እየዞርሁ ስሜ በተቀጠሰበት ፖስት ስር ሁሉ የልብ ቅርጽ ሳርከፈክፍ ብውል ደስ ይለኝ ነበር! በቀሪው ዘመኔ ከዚህ የተሻለ ላገለግላችሁ በጎ ምኞት አለኝ ! ብዙ ሰላም እና እና የተትረፈረፈ ጸጋ ላገራችን !


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19