Get Mystery Box with random crypto!

#አልመጣምን_ምን_አመጣው ?? . . ዛሬ ነበር የቀጠርሽኝ፤ እዚህ ነበር 'ናልኝ' ያልሽኝ። ፀሃይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#አልመጣምን_ምን_አመጣው ??
.
.
ዛሬ ነበር የቀጠርሽኝ፤
እዚህ ነበር "ናልኝ" ያልሽኝ።
ፀሃይ ስትደምቅ በስተምስራቅ ስትፈካ በሀገሩ፣
ከወፍ ጋራ እኩል ሲያዜም ሲዘማምር ጫካ ዱሩ።
የእግዜር በጎች ከልጆች ጋር በየመስኩ ሲሯሯጡ፣
ስስ እንቦሶች ሽር ብንት ሜዳው መሃል ሲቃበጡ።

ያኔ ነበር "ድረስ" ያልሽኝ፤
እዚህ ነበር የቀጠርሽኝ።

እኔ አፍቃሪሽ ያንቺው ንጉስ፤
ናፍቆት ፍቅር እንደታቀፍኩ ከንጋት ጋር ጎህ ቀድጄ፣
የፀደይ ወር እቅፍ አደይ፤ ላፍቃሪ ሩህ ይዤ በእጄ።
ካልሺኝ ቦታ እንደደረስኩ ዙሪያ ገባው ባማትረው፣
ችላ ብለሽ ቀረሽ መሰል ቃልሽ ፍቅሬን ሰባበረው።

አንቺዬ..............፤
እንደ ቀላል እንደ ዘበት፤
"እመጣለሁ" ባለ አንደበት፤
ምን ይሉታል ቃልን ማጠፍ "አልመጣም"ን ምን አመጣው ?
አጀብ መቼም ወንድ መሆን ያልተነሳ እግርሽ ቀጣው።
ብዬ እያሰብኩ ስብሰለሰል እዚሁ ሆኜ ልቤ አረጀ፣
በትዝታሽ ሳቅ... እያለ ይኸው ጊዜም አብሮኝ ጃጀ።

         " አጀብ መቼም ወንድ መሆን !!! "

ዓቢይ ( @abiye12 )

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19