Get Mystery Box with random crypto!

#MinT የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ባለቤቶችን ለመደገፍና ለማበረታታት የሚያስችል አ | Birhan Nega

#MinT

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ባለቤቶችን ለመደገፍና ለማበረታታት የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አሳውቋል።

በሚኒስቴሩ የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል ሠላምይሁን አደፍርስ ተከታዩን ብለዋል ፦

" ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ሥራዎቻቸው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ ነው።

አሁን ላይ ደግሞ ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ኢንተርፕራይዝ መሆን እንዲችሉ ማበረታቻዎችን የያዘ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው።

አዋጁ ሥራ ላይ ሲውል ውጤታማ የሚያደርግ ነው።

ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን አዋጁ ለመጽደቅ የሚያስችሉ አስፈላጊ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል።

አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች ለመደገፍ ሚኒስቴሩ እያወዳደረ ይገኛል፤ ተወዳድረው ያሸነፉ ፈጣሪዎች የገንዘብ፣ የቴክኒክና የሥልጠና ድጋፎችን እያገኙ ነው።

የልማት አጋሮች አሸናፊ ለሆኑ ኃሳቦች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉበት ሥርዓትም ተዘርግቷል።

ሚኒስቴሩ አዳዲስ የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን ልጆች ከመደገፍ ባሻገር ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ልጆችም የሚወጡበት ሥርዓት እየዘረጋ ነው "

#ENA

@tikvahethiopia