🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#EtPL ቅዱስ ጊዮርጊስ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫውን ለማንሳት ተቃርቧል በኢትዮጵያ ፕ/ሊግ ቅዱስ | DStv Ethiopia

#EtPL

ቅዱስ ጊዮርጊስ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫውን ለማንሳት ተቃርቧል


በኢትዮጵያ ፕ/ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዲያ ሆሳዕናን ዛሬ ቀን 9:00 ሰዓት ይገጥማል።

በዚህ 29ኛ ሳምንት ጨዋታ ፈረሰኞቹ ከጨዋታው አንድ ነጥብ ካገኙ የሊጉን ዋንጫ ከጅምሩ ለ31ኛ ጊዜ እንደ አዲስ ከጀመረ በኋላ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ የሚያሳኩ ይሆናል።

ሀዲያ ሆሳዕና በበኩሉ ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ለማለት ይጫወታል።

በምሽት 12:00 ሰዓት ሲል ደግሞ ባህርዳር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ይጫወታሉ።

ባህርዳር በሂሳባዊ ስሌት አሁንም የሊጉ ሻምፒዮን የመሆን እድል አለው፤ ሁለቱን ቀሪ ጨዋታ አሸንፎ ፈረሰኞቹ በሁለቱ መረታት እና ከ20 በላይ ግቦችን ማስቆጠር ይጠበቅበታል።

ባህርዳር ከተማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ መድረክ መሳተፉንም አረጋግጧል።

የዛሬ የባህርዳር ተጋጣሚ ሀዋሳ ከተማ ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ የማለት ዕድልን ይዞ ጨዋታውን ያደርጋል።

ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና መቻልን 2ለ1 እንዲሁም ለገጣፎ ለገዳዲ ሲዳማ ቡናን 3ለ2 መርታት ችለዋል።

ፓኬጅ : ጎጆ

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የአገልግሎት ክፍያዎን ቀድመው በመፈፀም የE-16 ችግሮችን ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ቀድመው ያስተካክሉ!

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች  ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!

https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfservice #EthiopianPremierLeague