🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ | DW Amharic

የሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ በብሔረ ብጹአን አፄ መልከዓ ሥላሴ ገዳም የታጠቀ ቡድን እየሰለጠነበት ነው በሚል ከጥር 22 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በንጹሀን ላይ ግድያና የአካል ጉዳት ደርሷል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ኢሰመጉ አስታወቀ። ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የገዳማቱ መናኝ መነኮሳትም የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈጸሙባቸው የአካባቢው አርሶ አደሮችም የግብርና ስራቸውን መከወን እንደተቸገሩ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ መቻሉን ገልጿል ።ኢሰመጉ ተኩሱን ሸሽተው የሚሄዱ ሰዎችም ተምቻ ተብሎ በሚጠራው በአካባቢው በሚገኝ ወንዝ ለጎርፍ አደጋ መጋለጣቸውንም ፣ መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር እና የማስከበር ሃላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ በሚል ባወጣው በዚሁ መግለጫ ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣ ያለው ሰዎችን አስገድዶ መሰወር በአፋጣኝ ሊቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ አሳሰበ። ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በተለይ በአዲስ አበባ ፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ጥቆማዎችን መሰረት አድርጎ ባደረገው ክትትል «በርካታ የአስገድዶ መሰወር ድርጊቶች መከሰታቸውን» አረጋግጫለሁ ብሏል።
የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮጳ የብዙ ሰዎችን ሕይወት ያጠፋ ጦርነት መሆኑ ተዘገበ ። አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ መረጃ ሰነድ ከ354 ሺህ በላይ የሩስያና የዩክሬን ወታደሮች በጦርነቱ ተገድለዋል ወይም ደግሞ ቆስለዋል ይላል ።
ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4SDkR?maca=amh-RED-Telegram-dwcom