🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#መግለጫ የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ፥ - 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማደናቀፍ | ገራዶ ሚዲያ

#መግለጫ

የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ፥

- 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማደናቀፍ በህቡዕ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖችን ሴራ ማክሸፉን ገልጿል።

- በህቡዕ ተደራጅቷል በተባለው የአመጽና የግጭት ቡድኖች ላይ በተደረገ ክትትል፤ አደረጃጀታቸው፣ አመራሮቹ፣ ለጥፋት ተልዕኮው የተዘጋጁ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ቁሶች፣ የገንዘብ ድጋፍና ዝውውር የተደረገባቸው ማስረጃዎች፣ ተልዕኳቸውን የተመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችና ማስረጃዎች ተጠናቅረው እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ብሏል።

- በህቡዕ የተደራጁት ቡድኖቹ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የተደራጁ ናቸው።

- ቡድኖቹ ሀገራዊ ምርጫውን ለማደናቀፍ ያወጡትን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ከአንድ አንድ የመንግሥት የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር አባላት እና አመራሮች ጋር ምስጢራዊ የሆነ ግንኙነት በመፍጠር ኢላማ የተደረጉ ቁልፍ አመራሮችን ለይቶ በመግደል ሀገራዊ ትርምስ ለመፍጠር የሚያስችል ሴራ በመጠንሰስ በድብቅ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል ብሏል።

* ሙሉ መግለጫው ከስር ተያይዟል፤ ያንብቡት!
https://telegra.ph/መግለጫ-05-06