Get Mystery Box with random crypto!

ፊል18 ላይ #አለቅሳለሁ ይለናል ይህን ጨካኝ ሰው ያስለቀሰው ነገር ለመስቀሉ ጠላት የሆነው ምልልሳ | ወንጌል ይለዉጣል📖

ፊል18 ላይ #አለቅሳለሁ ይለናል ይህን ጨካኝ ሰው ያስለቀሰው ነገር ለመስቀሉ ጠላት የሆነው ምልልሳቸው ነው ይህም ምልልስ ለሰው ፅድቅን ሚያመጣ ሳይሆን #ሞት የሆነ መጨረሻ ስላለው ነው።19 አንድ አባባል አለ "ለመኖር ስትል ብላ እንጂ ለመብላት ስትል አትኑር" ሚል ሆዳችን ጌታ ከሆነ ለሱ እንገዛለን በጣም ሚከብደው ቃል እዚህ ክፍል ላይ

"ክብራቸው በነውራቸው ነው" ሚለው ነው ዛሬ ላይ እንደ ክብር የያዝነው ነገር ምንድነው እግዚአብሔር ነውር ያለው እኛ ግን ክብራችንን አውልቀን ክብር ያረግነው ነገር ምንድነው መፀሐፍ ሮሜ 8:33 ላይ"የሚያፀድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኮንንስ ማነው?"ይላል ስለዚህ እግዚአብሔር የኮነነውን ነገር ክብራችን ሊሆን ይገባልን እንደ እነዚህ ያሉትን ሰዎች "አሳባቸው ምድራዊ ነው" ይላቸዋል ከምድር ያላለፈ ሰው ደግሞ የሰማዩን ክብር አያይም እግዚአብሔር ያለው ይሁን ለማለት ለእርሱ ፈቃድ የተገዛን ሰዎች መሆን ይገባናል እግዚአብሔርን ለሚወዱ እንዳሳቡም ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ ይላል ፍቅራችን ሚታየው በአክብሮታችን ነው የዛኔ ታማኝ ከሆነው ጌታ የእምነታችንን ፍሬ እንቀበላለን ስለዚህ ለክርስቶስ ሕይወት እንጨክን!