Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛው(ጌት) ፡-' ስለ ሴቶች ብቁነት ምን ታስቢያለሽ? ... ሴትነት ላንቺ ምንድነው?' ተጠ | ቅኔ ያለው ትውልድ

ጋዜጠኛው(ጌት) ፡-" ስለ ሴቶች ብቁነት ምን ታስቢያለሽ? ... ሴትነት ላንቺ ምንድነው?"

ተጠያቂ(ትዙ)፡- "ለኔ ሴትነት ከሁለቱ የሰው አፈጣጠር አይነቶች መሀል አንዱ_ብቻ ነው የተለየ ዕይታ የለኝም። ስለዚህ ሴት ልጅ ከባህል ተፅዕኖ ፣ ከኃላቀርነት እና ከሌሎች ጎጂ ነገሮች ውጪ ሴት_በመሆኗ_ብቻ!? በተፈጥሮዋ በምንም ነገር በርትታም ሆነ ሰንፋ ከሆነ የሸክላ ሰሪው አፈጣጠር ምድርን ምናልባት በአይነት ጣዕም የመስጠት ጉዳይ ብቻ ነው!
ብዬ ነው ማስበው ስለዚህ ተፈጣሪ በተፈጥሮ ሲፎካከር ማየት ሁለት ፈጣሪ ያለው እየመሰለው የመሞኘት ጉዳይ ነው የሚመስለኝ። ሴትነት ለኔ የፈጠረኝ አካል ሲፈጥረኝ ያሰበውን ያንን ነገር መኖር ነው ብዬ ነው የማስበው በሱ በጣም አምናለሁ።በፍጥረት ሁሉ ላይ ያለኝም ምልከታ የፈጠረኝ አካል ምን በዛ ውስጥ አይቶ ነበረ ነው ስለዚህ ሴትነትም, ሁለት ሴትና ወንድ ብሎ ሲፈጥር የፉክክር ሳይሆን የጣዕም/የአይነት ጉዳይ ነው ብዬ ስለማስብ እኔ ውስጥ የታየውን ጣዕም እና አይነት መኖር እንጂ የፉክክር ወይንም ደሞ የሌላኛው አይነት የተሻለ እንደሆነ የበረታ እንደሆነ በማሰብ ወደዛ ማዘንበል ለኔ ከተፈጥሮ ወይም የእኔን ትልቁን ሀይል የሚያውቀው የፈጠረኝን_አካል "አይ በኔ ውስጥ አታውቅም ፤ በኔ ውስጥ የሚያምረው ያኛው ነው"ብሎ እንደማረም ነው። ስለዚህ እሱ ያየውን ነሽ የተባልኩትን መኖር ነው ፤ እንዳልኩት የባህልን የኃላቀርነትን ምናምን ጉዳዮች ሳያካትት ሴትነት በተፈጥሮ ያለኝ እይታ ይሄ ነው ፤ ሌላው ባህልና ሌሎች ነገሮች የፈጠሩት ተፅዕኖ ተፈጥሮን_በአግባቡ_ካለመገንዘብ የመጣ ነው ብዬ ነው የማስበው።"

(ቅዳሜ,መስከረም 9,2013 ... ከተሰናዳው አስኳላ መዝናኛ)

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!