Get Mystery Box with random crypto!

…………… …… ……… አንደኛ ፤ ታምሪን የሚባለው ዓለም አቀፍ ነጋዴ በዘመኑ ሀብታም የነበረና | ቅኔ ያለው ትውልድ

…………… ……

……… አንደኛ ፤ ታምሪን የሚባለው ዓለም አቀፍ
ነጋዴ በዘመኑ ሀብታም የነበረና በቀይ ባሕር አካባቢ ባለው የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተፅእኖ የነበረው ሰው ነው ፣ በዚያን ዘመን አምስት መቶ ሃያ ግመሎችና ሰባ ሦስት መርከቦች በቁጥጥሩ ስር የነበረው ሰው ነው ፤ ከንግሥት ሳባ ጋርም ቅርብ ግንኙነት ነበረው ፤ እንዲያውም የንግስተ ሳባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልንለው የምንችል ይመስለኛል ፣ ስለአካባቢው ሁኔታ በየጊዜው ለንግስተ ሳባ ያስታውቅ ነበር ፤ ታምሪንየሰሎምንን የተለያዩ ስራዎች እያስታወሰ
ይደነቅና ለንግስተ ሳባም ይነግራት ነበር ፤ ማናቸውንም ነገር ሁሉ የሚፈፅመው በመመካከር ነበርና ሹማምንቱ ሁሉ ቃሉን ይቀበሉት ነበር ፤ የሰሎሞንን ጥበብ የተሞላበት አስተዳደርና የአገሩንም ሰላም ሁሌም ይነግራት ነበር ።

ሁለተኛ ፦ ፤ ንግስተ ሳባ ከታምሪን በምትሰማው ነገር ሁሉ ልብዋ ለእውቀት ተነሣሳ ፤ ወደሰሎሞንም ሄዳ እውቀትን ለመገብየት ቆረጠች ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብም የሚከተለውን ተናገረች:-

"ወገኖቼ ! ነገሬን አድምጡኝ ፤ እኔ ጥበብን እሻለሁ ፤ ልቤም እውነትን ትፈልጋለች ፤ በጥበብም ፍቅር ተነድፌአለው ፤ በጥበብ ገመዶችም ተይዣለው፤

……መንግስት ያለ ጥበብ አይቆምም ፣ ሀብትም ያለ ጥበብ አይጠበቅም፣. . . እኔ ጥበብን እፈልጋታለው . . ዱካዋን
እከታተላለሁ፤. . .እንፈልጋታለን ፣ እናገኛታለን ፣ እንወዳታለን . . የጥበብም ክብር ጠቢብን ማክበር ነው "

{ፕሮፌሰር መስፍን ወለደማርያም ፣ እንዘጭ !እምቦጭ!የኢትዮጵያ ጉዞ ከሚለው መፅሐፍ ከገፅ 99- 100 የተወሰደ}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!