Get Mystery Box with random crypto!

…………… «ማኅበረሰቡ አንዲትን ሴት 'የብረት መዝጊያ' የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ፣ የብረት መ | ቅኔ ያለው ትውልድ

……………

«ማኅበረሰቡ አንዲትን ሴት "የብረት መዝጊያ" የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ፣ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም! ስለዚህ የነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት፣ አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሮዋንም ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከህፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል።

እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነፅሁፉ፣ በፊልሙ አእምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኑሯል። ከመራመዷ በላይ የአረማመዷንና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትሰበክ ኑራለች።
ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱ ሴቶች ይልቅ፤ ከየትም ባገኟት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው፣ እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት። እግራቸው ከለሰለሰ በኋላ፣ አዝሎ የሚያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ። ...

ለብዙኃኑ ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ አገርን ያቆመ ሳይሆን፣ ሴትነትን የገፋ መስሎ ነው የሚታያቸው። ለዚያ ነው በሥራ ስለደደረ የሴት መዳፍ፣ ዘፋኙም መዝፈን፣ ገጣሚውም መግጠም የማይወደው። ድንጋይ ፈልፍሎና እምነበረድ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት ሴት ሐውልት የሚያቆመውን ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው፣ በሥራ የጎለደፈ ሆኖ ታገኘዋለህ።
ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሴት በሆነበት አገር፣ ሴቶች እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ ላይ እንዲያስቀምጡት በማድረግ፣ ለውጥ ጠብ አይልም፤ እንዲሠሩ ማደፋፈር፣ እጅ ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት!!» ...

{ከለታት ግማሽ ቀን. . አሌክስ አብርሃም }


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!