Get Mystery Box with random crypto!

እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያዬ እንደምን አደራችሁ መራሒቶች እስኪ አንባቢ ሁኚ!! በ | Merahit Club / መራሒት ክበብ

እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያዬ
እንደምን አደራችሁ መራሒቶች

እስኪ አንባቢ ሁኚ!!

በዙሪያችን ያሉ ሰወችን ስለንባብ ብንጠይቅ ከሚያዉቁት:ካዩትና በህይወታቸዉ ከገጠማቸዉ የከተቡትን ያጋሩናል።ነፍሳቸዉ በማንበብ አዉታር የተቃኘች ጀግኖች ድምዳሜ ግን ንባብ የህይወት እጅግ ምርጥ ነገር መሆኑን ነዉ።ሴት መሆን ምስጢር ነዉ!ይህን የፈጣሪ ፀጋ በመፃህፍት መሰረት ላይ ስትገነቢ አንቺ እንቁ ሔዋን ትሆኛለሽ።
-አንባቢ ሴት ምርጫዋን ታዉቃለች!
-አንባቢ ሴት ንግግሯ ተወዳጅ የማይሰለችም ነዉ!
-አንባቢ ሴት አዕምሮዋ በእዉቀት የተሞላ ነዉ!
-አንባቢ ሴት በመፃህፍት መርከብ ላይ አለምን ትዞራለች!
-አንባቢ ሴት ነገዋን ዛሬ ላይ ታየዋለች!
-አንባቢ ሴት ለችግሮቿ መፈትሔ ትፈልጋለች እንጅ አትሰበርም!
ለአንቺ የማይሆን የከፍታ ቦታ የለም።ጠንካራ ሴት ከሆንሽ ትችያለሽ።ደራሲያን ብዕራቸዉን ጨምቀዉ እዉቀትን የከተቡባቸዉ መፃህፍት የመንገድሽ ድልድይ ናቸዉ።በእቅድ የታጀበዉ ቀንሽ ላይ ለመፃህፍት የሚሆን ጊዜ ብትጨምር በእርግጠኝነት ታተርፊበታለሽ።በማንኛዉም ርዕሰ ጉዳይ ላይ መወያየት የምትል ሴት ለመሆን መፅሀፍት አንደበትሽ ይሆናሉና ምርጥ ጓደኞችሽ አድርጊያቸዉ።
ትችያለሽ
መልካም ቀን ጀግኒት

#ብሩህ_ቀን_ይሁንልን
#መራሒት
#እኔ_የእህቴ_ጠባቂ_ነኝ