Get Mystery Box with random crypto!

ተማሪ መመገብ ያልቻሉ ዩኒቨርስቲዎች እየበዙ ነው ዲላ ዩኒቨርስቲም የምግብ በጀት እጥረት እንደገ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ተማሪ መመገብ ያልቻሉ ዩኒቨርስቲዎች እየበዙ ነው

ዲላ ዩኒቨርስቲም የምግብ በጀት እጥረት እንደገጠመው ገልቷል፡፡

ቀደም ሲል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተመሳሳይ እጣፈንታ እንደገጠመው መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አብዛሃኛዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለመመገብ ችግር እንደገጠማቸው በዚህ ዘገባችን ስር ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡

ለማሳያነትም ድላ፣ ሀዋሳ እና አምቦ ዩኒቨርስቲ በበጀት እጥረትና በምግብ ግብኣት ችግር ተማሪዎቻቸውን መመገብ እንዳልቻሉ ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡

ዲላ ዩኒቨርስቲው በለጠፈው ማስታወቂያ እንደ ሀገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረትና የምግብ ዋጋ መጨመር ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት አስቆጥሯል ብሏል፡፡

ተማሪዎቼ ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ አትክልት እንዲመገቡ እያደረኩ ነው ብሏል፡፡

በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦ እንዲሟላልን ጠይቂያለሁ ያለው የድላ ዩኒቨርስቲ የአቅርቦት ሁኔታው እስከሚስተካከል በትዕግስት ጠብቁ ሲል አስታውቋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT