🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox

Logo of telegram channel orthodoxholyfathers — የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox
Logo of telegram channel orthodoxholyfathers — የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox
Channel address: @orthodoxholyfathers
Categories: Religion
Language: English
Subscribers: 465
Description from channel

This channel's aim is to help us learn from the spritual life of holy fathers .
ከቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች እንማር ዘንድ የ ተዘጋጀ channel ነው።

ከቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች group https://t.me/joinchat/FXPZVEUP8KLHay0v0d0LuQ
አስተያየት ካላቹ በ @Wiseholyfathers_comment ይላኩልን።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages 3

2021-05-17 06:30:08 ​​"እመቤቴ ሆይ በአንቺ ጸሎት በልጅሽ ቸርነት ከታመንሁ ሰማይ ወፍጮ ምድር መጅ ቢሆኑ ሁለቱም ሊያጠፉኝ ቢፈልጉ አንዳች ሊያደርጉኝ አይችሉም"

ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


@wiseholyfathers
አስተያየት ካላቹ በ @Wiseholyfathers_comment ይላኩልን
40 views03:30
Open / Comment
2021-05-15 12:34:31 ​​ በምድር ላይ የምንቆየው የዕድሜ ልክ ቆይታ በዘላለማዊው ሕይወት ካለው የዓይን ጥቅሻ አፍታ ጋር እንክዋን እኩል አይሆንም:: የዚህ ምድር ቆይታ እንግዲህ ለዚያኛው የሚያበቃን ነው


አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ


@wiseholyfathers
አስተያየት ካላቹ በ @Wiseholyfathers_comment ይላኩልን
113 views09:34
Open / Comment
2021-05-14 06:25:29 ​ዓሣ ከውኃ ወጥቶ ከቆየ ወዲያው እንደሚሞት ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ሕይወቱ ከወጣ እንደዚሁ ይሞታል፡፡ ዓሣው ቶሎ ተምልሶ ወደ ውኃው ሲገባ እንደሚድን ሰውም በንስሐ ቶሎ ሲመለስ እግዚአብሔር የይቅርታውን በር ይከፍትለታል፤ ስለዚህ ንስሐን እንደ ቀላል ነገር አትቁጠረው።

@wiseholyfathers
አስተያየት ካላቹ በ @Wiseholyfathers_comment ይላኩልን
124 views03:25
Open / Comment
2021-05-11 19:46:27
43 views16:46
Open / Comment
2021-05-09 09:03:22 ​​እመቤታችን ተወለደች ማለት ጌታ ሊወለድ 15 ዓመት ቀረው ማለት ነው:: እግዚአብሔር ከሴት የተወለደ ልጁን ሊልክ የዘመኑ ፍጻሜ ቀረበ ማለት ነበር። እግዚአብሔር ሃና እና ኢያቄምን ሳይወልዱ ያዘገያቸውም ለዚህ ታላቅ ክብር እንዲበቁ ነበር።
ቀድመው ልጅ ቢወልዱ ኖሮ ይህችን የፍጥረት ደስታ የሆነች ልጅ አይወልዱም ነበር:: የእርስዋ የልደት ቀን የፍጥረት ደስታ ቀን ነው::

ክርስቶስ ፀሐይ ከሆነ የዛሬው ዕለት ሰማይዋ የተዘረጋችበት ዕለት ነው።

ክርስቶስ የሕይወት ውኃ ከሆነ ዛሬ ምንጭዋ የፈለቀችበት ዕለት ነው።

ክርስቶስ መድኃኒት ከሆነ ዛሬ የመድኃኒቱ ሙዳይ የተገኘችበት ዕለት ነው::

ወንጌል በመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ይላል። በእመቤታችን መወለድ ምን ያህል ሰዎች ደስ ይላቸው ይሆን? የእመቤታችን ልደት በብዙ ሀገራት ብሔራዊ በዓል ሆኖ ይከበራል።

እኛም በሊባኖስ ተራሮች (አድባረ ሊባኖስ) መወለድዋን በማሰብ ከደጅ ወጥተን ቅድም አያቶችዋ በጨረቃ ተመስላ በህልማቸው ያዩአትን የጨረቃችንን (በግሪኩ ሶልያና) ልደት ጨረቃን እያየን እናከብራለን። የልደትዋ ቀን ልደታችን ነው!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት ልደታ 2012 ዓ ም


@wiseholyfathers
አስተያየት ካላቹ በ @Wisecomment_bot ይላኩልን
396 views06:03
Open / Comment
2021-05-06 15:04:47 ​​እናቴ ማርያም ወላዲተ አመላክ እመ ብርሃን ሆይ!

በዚህ ዓለም ዕውነተኛ
ዘመድ ጓደኛ ወገን እንደሌለኝ ታውቂያለሽ
እናቴ ተስፋዬ አመባ መጠጊያዬ አለኝታዬ ክብሬ አንቺ ነሽና

ፀጋሽን

ሰላምሽን

ረድኤትሸን ፣

በላዬ ላይ እንደ ክረምት ውሃ አዝንቢልኝ
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከሰራሁት ኃአት መተላለፍ
ከወላጆቼ በደልና መተላለፍ ከወገኖቼ በደልና ግፍ ፣ አንቺ በከበረው ቃል ኪዳንሽ እጠቢኝ " ንጹህ አድርጊኝ : ተናግሬ ማሳመን በተሳነኝ ጊዜ አንቺ አንደበት ሁኝልኝ። የአብርሐም እንግድነት፣ የይስሐቅ መዓዛ ፣ የያዕቆብ መሠላል ድንግል ማርያም ሆይ! ዓለሙ ሁሉ ለኔ ባዳ ሆኖብኛል ፣ ብወጣም ብወርድም hድካም እና ከትዝብት በስተቀር ሊሆንልኝ አልቸለምና ልጅሽበሠጠሽ በhበረው ቃል ኪዳንሽጉዶሎዬን ሞልተሽ ከውርደት አድኚኝ : ለቤተሰቤ ለወገኔ ለሀገሬ ለፍጥረት በሙሉ ጠቃሚ አድርጊኝ።

እናቴ ጸጋ በረከትሽና ረድኤትሽ ለዘለዓለሙ አይለየኝ አሜን


@wiseholyfathers
አስተያየት ካላቹ በ @Wisecomment_bot ይላኩልን
629 viewsedited  12:04
Open / Comment
2021-05-04 18:47:20
372 views15:47
Open / Comment
2021-05-02 08:00:08 የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox pinned «​​በስመአብ ወ ወልድ ወ መንፈስቅዱስ ፩ አምላክ አሜን ክርስቶስ ተንስዐ እሙታን በዐብይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምዝእይሴ ኮነ ፍስሀ ወ ሰላም "ከሲዖል እጅ እታደጋቸዋለሁ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ ሞትሆይ ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሞትሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ርህራሄ ከዓይኔ ተሰወረች" ሆሴ ፲፫፡፲፬ "እንደተናገረ ተነስቷል…»
05:00
Open / Comment
2021-05-02 03:50:44 ​​በስመአብ ወ ወልድ ወ መንፈስቅዱስ ፩ አምላክ አሜን
ክርስቶስ ተንስዐ እሙታን
በዐብይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምዝእይሴ
ኮነ
ፍስሀ ወ ሰላም
"ከሲዖል እጅ እታደጋቸዋለሁ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ ሞትሆይ ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሞትሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ርህራሄ ከዓይኔ ተሰወረች" ሆሴ ፲፫፡፲፬

"እንደተናገረ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም" ማቴ ፳፰ እስከ ፍፃሜው ይነበብ

"እርሱ ግን አትደንግጡ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ ተነስቶአል በዚህ የለም" ማር ፲፮ እስከ ፍፃሜው ይነበብ

"ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ እንዲህ አሉአቸው ሕያውን ከሙታን ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም" ሉቃ ፳፬ እስከ ፍፃሜው ይነበብ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርት ውድስት ቅድስት በዓለ ትንሳዔው በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን

"ለመስቀልከ ንሰግድ ወለ ትንሳዔከ ቅድስት ንሴብህ ኩልነ ይእዜኒ ወዘልፈኒ"

ጌታዬ ሆይ ክቡር የሚሆን የመቃብርህ ጠባቂዎች ከድንጋፄ የተነሳ የትንሳዔህ ግርማ የገለባበጣቸው በሦሥተኛው ቀን ከሙታን ተለይተህ ለተነሳኽው ትንሳዔህ ሰላምታ ይገባል" (መልክዐ ኢየሱስ ለትንሳዔከ ቀዳማይ)

"ስለፍፁም ሃይማኖት በክብር ለሞቱ ቅዱሳን ሁሉ የትንሳዔያቸው መተማመኛ ለሆነው ትንሳዔህ ሰላምታ ይገባል"(መልክዐ ኢየሱስ ለትንሳዔከ ካልዕ)

"በአርብ ሙታን እና ህያዋን በድኅነታቸው ተደሰቱ በእኁድ ደግሞ በህይወት ያሉ አረጋገጡ እናም ትንሳዔያቸው በክርስቶስ ስጋ እንደሆነ አወቁ" (የኮፕቲክ ቤተክርስቲያ የመጋቢት፳፱ ስንክሳር )

"በእውነት እኛ ኦርቶዶክሳውያን የዘመናት ንጉስ ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ ብለን እናምናለን ከእኛ ንጉስ አማኑኤል ከሞት መነሳት በኋላ ሁሉን ደስታ እና ሀሴት እግዚአብሔር"(የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የበዓለ ሃምሳ የሌሊት ምስጋንና)

"የእኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እና ጥበቡን እኛ ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ ብለን እናመሰግነዋለን እናም እሱ እንደተናገረው ነብያትም እንደተናገሩት በመቃብር ተቀበረ ከሦስት ቀንም በኋላ ተነሳ" (የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የበዓለ ሃምሳ የሌሊት ምስጋና)

"የደስታ እናት ድንግል ማርያም ተደሰቺ በእውነት ያንቺ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷልና ዛሬ ሁላችን እንደሰት ደስተኛም እንሁን ምክንያቱም የንጉሦች ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷልና"(የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የበዓለ ሃምሳ የሌሊት ምስጋና)

"ጥበበኛው ሉቃስ እና ተወዳጁ ዮሐንስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷልና በእውነቱ ወንጌልን ስበኩ ክርስቶስ ሆይ የማጠልቅ ፀሀይ ሆይ ና እኛም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል ብለን እናመስግንህ"(የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የበዓለ ሃምሳ የሌሊት ምስጋና)

" ሞት በሞት ተያዘ ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ እሱ በመቃብር ሆኖ ህይወትን ሰጠ"(የምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን ስንክሳር የፋሲካ ስንክሳር)

"ይሄ የትንሳዔ ቀን ነው ሁላችንም በበዓሉ እናብራ(እንድመቅ) ሁላችንም እርስ በእርስ እንተቃቀፍ ሁላችንም የጠላነውንም ቢሆን እንኳ በትንሳዔው ይቅር እንበል ወንድሞቼ ተባብለንምእንጠራራ"(የምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን ስንክሳር የፋሲካ ስንክሳር)

"ሞትሆይ መያዝህ የትአለ? መቃብር ሆይ ድል መንሳትህ የትአለ? ክርስቶስ ሲነሳ እና ሲነግስ ከስልጣንህ ተሻርክ፣ክርስቶስ ሲነሳ አጋንንት ወደቁ፣ ክርስቶስ ሲነሳ መላዕክት ተደሰቱ"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

"ትላንት ከእርሱጋ ተሰቅዬ ነበር ዛሬ ከእርሱጋ እከብራለሁ ትላንት ከእርሱጋ ሞቼ ነበር ዛሬ ከእርሱጋ ህያው እሆናለሁ ትላንት ከእርሱ ጋ ተቀብሬ ነበር ዛሬ ከእርሱ ጋር እነሳለሁ"
(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ

"ምድር በክርስቶስ ደም ታጥባለችና ፋስካን ታደርጋለች"

(ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊ)
ለሁላችሁም መልካም የፋሲካ በዓል ወንድሞቼ እኅቶቼ።
103 views00:50
Open / Comment
2021-04-29 19:43:25 ​​ወላዴ አዕላፍ የኔታ ጥበቡ ታዬ
የፍቅር የትሕትና የጸሎት ፤የትሕርምት ሰው ታላቅ አባትና መምህር በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በደራ ወረዳ ሐሙሲት ደብረ ምሕረት ዛራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የቅኔ ና የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር ታላቅ ጸሎተኛ አባታችንን አረፉብን ፡፡
የእሼ ፍሬ ብቻ እየበሉ ዐቢይ ጾምን ይጾሙ የነበሩት የኔታ በአጽንዖ በዓት ሳይፈተኑ ለአንዲት ቀን እንኳን ከጥንታዊው ዛራ ሚካኤል ሳይለዩ የኖሩ ድንቅ ባሕታዊ ናቸው የኔታ። እኚህን ታላቅ ሊቅ በማጣታችን ለቤተክርስቲያን ታላቅ ሀዘን ነው።

ተስፋችን አጽናኛችን ባሪኪ አባታችንን የነጠቀን ዘመን ምንኛ ጨካኝ ነው።
ከ 63 ዓመታት በላይ በመምህርነት ቆይተዋል በእነዚህ ዓመታት ያፈሯቸውን ደቀ
መዛሙርት በቁጥር ይህን ያህል ማለት ያስቸግራል፡ ሰባኪያነ ወንጌል ፤የጉባኤ
ቤት መምህራን ፡ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችንና ሊቃነ ጳጳሳትን
አፍርተዋል፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስንና አቡነ መርቆርዮስም ብፁዕ አቡነ ኤልሣዕ፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ በርናባስ እና ሌሎችም ከ9 በላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ከሊቃውንት ደግሞ መምህር ባሕታዊ ኪዳነ ማርያም፣ ሊቀ ሊቃውንት አባ ዕዝራ ሐዲስ፣ ሊቀ ሊቃውንት ትሕትና እና ሌሎችም በመላ ሃገሪቱ አንቱ የተባሉ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በርካታ አንጋፋ ሊቃውንት ይጠቀሳሉ።

የእርሳቸው ፍሬ ናቸው ። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያ “ የፍቅር የትሕታነ የጸሎት ፤የትሕርምት ሰው ታላቅ አባትና መምህር “ ይሏቸዋል።
ከእርሳቸው በረከት ለመቀበል ከመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም ከውጭ ሃገራት ጭምር ምእመናት ይመጣሉ ሰላም ለኪን ጸልየው ድዊያን ፈወሰው የተጨነቁትን አረጋግተው በፍቅር ይሸኟቸዋል።
የአብነተ ተማሪወች የቅኔ ትምህርትን ለመጀመር ካሰቡ የትምህርቱ ሚስጥር እንዲረዱት ከእርሳቸው ጉባኤ ደርሰው ለመባረክ ከኤርትራ ምድር ድረስ ይመጣሉ።
ወላዴ አዕላፍ የኔታ ጥበቡ ታዬ ዕውቀታቸውን ብቻ ሳይሆን መልካም ምግባራቸው ሕይወታቸው አርአያነታቸው ለሁሉ አስተማሪ ነው፡፡


ኦ እግዚኦ አድህን ህዘበከ ወባርክ ርስተከ
75 views16:43
Open / Comment