🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ዛሬ ረፋድ ላይ በዋልታ ሬድዮ ሰላም ለእናንተ የSAFELIGHT INITIATIVE ውድ ቤ | SAFE LIGHT INITIATIVE

ዛሬ ረፋድ ላይ በዋልታ ሬድዮ

ሰላም ለእናንተ የSAFELIGHT INITIATIVE ውድ ቤተሰቦች

ዛሬ ረፋድ ግንቦት 25, ሐሙስ 2014 ዓ.ምወደ-ሥራ በተሰኘው የዋልታ ራድዮ ፕሮግራም ዝግጅት ላይ ፡ እንግዳ ሆነን የምንቀርብ ሲሆን ፥
ለእናንተ ውድ ቤተሰቦቻችን እና መላው የሀገራችን ልጆች ፡ በዋልታ-ራድዮ ሞገድ FM105.3 በልዩ አቀራረብ አብረን ከመታደም በላይ ፡ ስለ ወጣቶች ፣ ስለ ሰፊው ታዳጊ የህብረተሰባችን ክፍሎች ፣ ስለ ሴቶች እና ሰራተኛው የህብረተሰባችን ክፍል ከተለያዩ ምልከታዎች አንፃር ፤

በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ሙያዊ ስነምግባር ፡ በሞራል ፡ ተስተናጋጅ ማንነትና የስራ መስክ ቅኝት ፡ ስነልቦናዊ እንዲሁም ሙያዊ ብቃት ብሎም ተደራሽነት የመሣሠሉትን አጀንዳዎች ከተለያዩ ወቅታዊ|ሀገራዊ|አህጉራዊና አለምአቀፋዊ የSAFELIGHT INITIATIVE ምልከታዎቻችን ጋር ፥ ጊዜ በፈቀደ መልኩ በስፋትና በጥልቀት ከመላው የዋልታ ሬድዮ ውድ አድማጮች ጋር የምንጨዋወትበትና እጅግ ጥሩ ጊዜ የምናሳልፍበት እንደሚሆን ፡ ፅኑ እምነታችንን ከወዲሁ ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።


ይጠብቁን

@SafeLightofficial