🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ከ3 ሺ በላይ የሚሆኑ በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማገናኘቱ | Crazy jocks 😜😂

ከ3 ሺ በላይ የሚሆኑ በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማገናኘቱን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምክትል ዋና ፀሀፊ አቶ እንግዳ ማንደፍሮ ለአሀዱ እንዳሉት ከአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበርና በክልሉ ከሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን የማገናኘት ስራ እየሰራ ነው፡፡

ማህበሩ ከ 3 ሺ በላይ የሚሆኑ የተማሪዎችን መልክት በማስተላለፍ እና የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀምም በስልክ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማገናኘት ስራ ተሰርታል ያሉት ዋና ፀሀፊ አቶ እንግዳ ማንደፍሮ ናቸው፡፡

ይህ ተግባር ቀጣይነት ያለው ሲሁን አሁን ላይ መንግስት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመነጋገር በክልሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችን የማስወጣት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡