Get Mystery Box with random crypto!

ጥሪ ለሰለምቴዎች በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 94:5-6 ከች | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ጥሪ ለሰለምቴዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

94:5-6 ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡ ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا

ሰለምቴዎች ታሪካቸው በተለያዩ "ፈተና" "ችግር" "መከራ" በብዙ ውጣ ውረድና ውስብስብ መንገድ ውስጥ ማለፉን በነገሩን ጊዜ የሚታወሰን "የጌታችን" ቃል ልባችን ውስጥ ሰርጾ ይገባል፦
94:5 ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡
فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا
94:6 ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا

"አል-ዑሥራ" ማለት "ችግር" "መከራ" "ጭንቀት" ማለት ሲሆን "ዩሥራ" ማለት ደግሞ "ምቾት" "ድሎት" "ገር" ማለት ነው፡፡ "ዑሥር" "ችግር" የሚለው ቃል ላይ "አል" ስለገባበት ማዕሪፋህ ይባላል "ማዕሪፋህ” مَعْرِفَة ማለት “አመልካች መስተአምር”definite article” ማለት ነው። "ዩሥራ" "ምቾት" የሚለው ቃል ላይ ደግሞ “አል” ስለሌለው "ነኪራህ" ይባላል፥ “ነኪራህ” نَكِرَة‎ ማለት "ኢ-አመልካች መስተአምር”in-definite article” ማለት ነው።

በዐረብኛ ሰዋሰው መሠረት "ማዕሪፋህ" የሆነ ቃል ሁለት ጊዜ ተደጋግሞ ከመጣ ሁለት ተደርጎ አይያዝም። "ማዕሪፋህ" "ማዕሪፋን" ከደገመ አንድ ነው። በተቃራኒው ግን ነኪራህ የሆነ ቃል ሁለት ጊዜ ተደጋግሞ ከመጣ ሁለቱም ይለያያሉ:-
94:5-6ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡ ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا

እዚህ ላይ "አል-ዑሥር" "ችግር" የሚለው ሁለት ጊዜ ቢደጋገምም "ማዕሪፋህ" ስለሆነ ሁለት ችግር መሆኑን አያሳይም፡፡ "ዩሥራ" "ምቾት" የሚለው "ነኪራህ" ሁለት ጊዜ በመደጋገሙ ምቾቶቹ ከችግር ቡኃላ በእጥፍ ሁለት ምቾት መሆኑን ይገልጻል ይህም በብዙ ሰሐቦች የተነገረ ሲሆን፦
አል-ሙወጣእ ኢማም ማሊክ ሐዲስ ቁ1288
ዑመር ኢብኑል-ኸጣብ”ረ.ዐ” ወደ ሮም በላከው መልእክት፦ "አንድ ችግር ሁለት ምቾትን አይረታም" ብሎ ፅፏል..
...فَكَتَبَ إِلَيْهِ عُمَرَ ابن الخَطَّاب... وإنّهُ لَنْ يَغْلِبَ عُسْرٌ يُسْرَيْنِ، وَأَنَّ اللَّهَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى يَقُولُ فِي كِتَابِهِ : { يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اصْبِرُوا وَصَابِرُوا وَرَابِطُوا وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ } .
ኢማም ቡኻሪ በኪታቡ ተፍሢር:-
قَالَ ابْنُ عُيَيْنَةَأَيْ مَعَ ذَلِكَ الْعُسْرِ يُسْرًا وَلَنْ يَغْلِبَ عُسْرٌ يُسْرَيْنِ
"ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡"
የሚለውን አንቀጽ አስመልክቶ: ኢብኑ
ዑየይነህ እንዲህ ብሏል፦ "አንድ ችግር ሁለት ምቾትን ሊያሸንፍ አይችልም፡፡"

አምላካችን አላህ አንድ "ችግር" ገልጾ ሁለት "ምቾትን" ማውሳቱ "ችግር" መቼም ቢሆን "ምቾትን" "ድሎትን" እንደማያሸንፍ ፍንትው አድርጎ ይገልጻል፡፡ ችግር ከኃላም ከፊትም በምቾት ተከቧል፡፡

ሰለምቴዎች ከክህደት ጨለማ አፈትልከው ወደ እምነት ብርሃን፣ ከውስብስብ የተረት አስተምህሮት እርቀው ጥልልና ጥንፍፍ ወዳለው አስተምህሮት፣ ከሥላሴ ቅዠትና አምልኮት ተላቀው በብቸኛውና ኃያሉ ፈጣሪ ፍቅር ስር መውደቃቸው የኅሊና እርካታ፣ ምቾትን፣ ደስታንና እፎይታን፣ የልብ መረጋጋትንም እንደሰጣቸው በሰማን ጊዜ የጌታችን ቃል ልባችን ውስጥ ሰርጾ ይገባል:
48:4 እርሱ ያ:- ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ በምእምናን ልቦች ውስጥ “እርጋታን” ያወረደ ነው፡፡
هُوَ الَّذِي أَنزَلَ السَّكِينَةَ فِي قُلُوبِ الْمُؤْمِنِينَ لِيَزْدَادُوا إِيمَانًا مَّعَ إِيمَانِهِمْ ۗ


ሰሐቦች ሁሉ ከነብያችንﷺ እየሰሙ ሐዲስ ያስተላልፋሉ፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው “የአላህ መልእክተኛﷺ "ነገረኝ" "حَدَّثَنِي" ብለው ሐዲስ ያስተላለፉለትና የሰለመበትን ምክንያት ሙሉ ታሪኩን ያወሩለት ብቸኛው ሰሐቢይ ከክርስትና ወደ እስልምና የገባ ሰለምቴ ነበር፡፡ ይህም ሰሐቢይ፦ "አቡ ሩቂያህ ተሚም ኢብን-አውሥ አል-ዳሪይ" "ረ.ዓ" ይባላል፡፡ በእርሱ ታሪክ ሰሐቦች የተደነቁበት ነብያችንምﷺ ተደስተው ፈገግ እያሉ የነገራቸውን ሁሉ የተረኩለት ታሪክ ነው፡፡ "ሙሥሊም2942"

ከመስለማችሁ በፊትና ከኢሥላም ቡኃላ የኖራችሁትን ታሪክ ለሌላው በማጋራታችሁ ብቻ ለአማኞች ተምሳሌት ለበርካቶች ደግሞ ከሺርክ ጨለማ መውጫና ወደ ተውሒድ ብርሃን መግቢያ ሰበብ መሆን ይቻላልና የአስሐቡል የሚን ቤተሰቦችን በመናገር ታሪካችሁን ታካፍሉን ዘንድ ጋብዘናችኃል፡፡

46:13 እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ፣ ከዚያም "ቀጥ" ያሉ በነርሱ ላይ "ፍርሃት" የለባቸውም፡፡ እነርሱም "አያዝኑም"፡፡
إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

ከታች የተዘረዘሩትን ሊንኮች በመጫን ያናግሩን ታሪኮዎን ያጋሩን:-

የወሒድ ተማሪ
ወሥ-ሠላሙ ዐለይኩም

https://t.me/AzizAbrar

https://t.me/Quran_is_life_Sari_A

https://t.me/Ohanw9

https://t.me/Qelb_Seleem

https://t.me/OBintMahmud

https://t.me/Selmeta