በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤ እንደሚታወቀው በአስሓቡል የሚን ስር የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ከተጀመረ ወራቶችን አስቆጥሯል ። እርሱም የተለያዩ ከክርስትና ወደ እሥልምና የመጡ እህቶችና ወንድሞች የሒዳያ ሰበብ የሆነውን ታሪካቸውን ቀጥታ በድምጽ ወይም በጹሑፍ የሚገልጹበት ሲሆን ለዛሬ የኡስታዝ ካሊድ ክብሮም እንዴት ሰለምኩኝ ፦ ጥያቄ ቁጥር አንድ ይዘን ቀርበናል ፦ ወደ እሥልምና ለመግባት ሰበብ የሆነህ ሰዎች ናቸው ወይስ እውቀት ...!? በመጀመሪያ ሰበቡን ከመናገሬ በፊት አላህ የቀደረው ወይም አላህ ሽቶልኝ ነው ።አምላካችን አላህ ነው ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመራው ሰዎች ልቦቻቸውን ለቅን ጎዳን እስከከፈቱት ድረስ። በነበርኩበት እምነት ላይ ጥሩ አምላኪና ጥሩ የእምነቱ ተከታይ ለመሆን ሙከራ አደርግ ነበር። ሆኖም በትክክል መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጥረት ነበረኝ ከልቤም አነበው ነበር ። ሳነበው ግን በእውነት መቀበል ብቻ ሳይሆን ጥያቄዎችን በመጠየቅ መጽሐፉንም በመመርመር ነበር የንባብ ቆይታዬ በዙሪያዬም ሙሥሊሞች ነበሩ ስለ እሥልምና ባያብራሩልኝም ባይገልጹልኝም ነገር ግን የእሥልምናን ውበት የማይባቸው አንዳንድ ጓደኞች ነበሩኝ ። አላህ የከፈተልኝ እውቀት መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና ሳይንስን በተወሰነ ደረጃ መረዳት ምክንያታዊ ሰው መሆን ከንባብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከፍተኛ የሆነ ተጽኖ አላቸው ወደ እሥልምና ለመምጣት ። ያ ማለት ግን ሙሥሊም ወንድሞች ወደ ኢሥላም ለመምጣቴ አስተወጾ አላደረጉም ማለት አይደለም። የሁለቱም ውጤት ድምር ነው። ነገር ግን መጽሐፍን ማንበብ እና ቆም ብሎ ማሰብ ወዴት አቅጣጫ እየሄድኩኝ ነው የያዝኩትም ነገር እውነት ነው ወይስ አይደለም ..!? የውርስ ሃይማኖት ነው ወይስ የተፈጥሮ ብሎ በመመርመር ትልቅ ቦታ ነበረው እና አላህ ሲመራኝ በዚህ እውቀት ላይ መሠረት አድርጎ ነው ወደ ቅኑ ጎዳና የመራኝ ። ወደ እሥልምና ስገባም ሙሉ በሙሉ እሥልምናን አምኜ ክርስትናን የውርስ እምነት መሆኑን የተረዳሁት በሰው ሳይሆን በእውቀት መሠረት ወደ እሥልምና ስለገባሁ ይመስለኛል ። ጥያቄ ቁጥር 2 ከቤተሰብህ እሥልምናን የተቀበለ ሌላ ሰው አለ.. ?ደግሞ በእምነቱ ዙሪያ ቤተሰቦችህ ምን አይነት አመለካከት አላቸው..!? የኡስታዝ ካሊድ ክብሮም መልስ ይቀጥላል..... ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ የተለያዩ ከክርስትና ወደ እስልምና የመጡ የሰለምቴዎችን ታሪክ ያገኙበታል ፦ የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :- AS_HABULE YAMlNE TUBE https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q በጹሑፍ ይቀርባል ¶ https://t.me/AshaBuleyamine/5125 ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ https://t.me/Selmeta አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች http://tiktok.com/@as_hbule አስተያየት ለመስጠት http://t.me//Ashabulyeminbot ለበለጠ መረጃ https://t.me/Quran_is_life_Sari_A አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች http://tiktok.com/@as_hbule የሠለምቴዎች መዝናኛ እና መማሪያ ግሩፕ 1.7K viewsedited 17:36