Get Mystery Box with random crypto!

ይችን ሙስሊም ሳትሆን እንደሙስሊም ለብሳ የፕሮቴስታንት ቲቪ ላይ እንደከፈረች አድርጋ ጥሩ ተውኔት | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ይችን ሙስሊም ሳትሆን እንደሙስሊም ለብሳ የፕሮቴስታንት ቲቪ ላይ እንደከፈረች አድርጋ ጥሩ ተውኔት የተጫወተችውን አጭበርባሪ ሳይ በሆነ ወቅት የገጠመኝ አጋጣሚ ትዝ አለኝና ላካፍላችሁ ወደድኩኝ።

አጋጣሚው እንዲህ ነበር። ከዓመታት በፊት በእጅግ አጫጭር ቀሚሶች ለብሳ የማውቃት ልጅን ሒጃብ ለብሳ አገኘኋት። በደስታ ደነገጥኩኝ እሷ ናት ወይስ አይደለችም ብዬ ተጠራጠርኩኝ። ሰላም ስትለኝ ነው እሷ መሆኗን እርግጠኛ የሆንኩት። ሙሉ ለሙሉ አለባበሷ የሙስሊም ነው። አለባበሷ አጉል ሰለጠንን እንደሚሉ እንደ አንዳንድ ሙስሊም ሴቶች እንኳን ግማሽ ሒጃብ አልነበረም። ማሻአላህ አልኳት ሰልማ እንደሆነ እርግጠኛ ሆኜ። እጅግ የሚያስደስተኝ ነገር ሰው ሰልሞ ማየት ነው።

የተወሰነ አወራኋት፤ በወሬዋ ግን ጥርጣሬ ፈጠረብኝ። አዲስ ሰለምቴ ስለሆነች ይሆናል ወሰድ የሚያደርጋት(ወሬዋ ወደ ኩፍር የሚሄድባት) ብዬ አሰብኩኝ። ውስጤ ግን ይሞግተኝ ያዘ። ለማጣራት ስሞክር እውነታው አስደነገጠኝ አስገረመኝም።

ልጅቱ አልሰለመችም፤ አለባበሷ ብቻ ነው የሰለመው። የተራቆቱ አጫጭር ልብሶቿን ጥላ ሒጃብ ከለበሰች ሁለት ዓመት ገደማ ሆኗታል። ምናልባትም አለባበሷን አትወደው ይሆናል። እንዲያ የለበሰችው ግን በዓላማ ነው። ዓላማዋም ሙስሊም መምሰል ነው። ሙስሊም ሳትሆን ሙስሊም መምሰል ምን ይጠቅማታል ትሉ ይሆናል። በመምሰል ውስጥ አንድም ሙስሊሞችን በቀላሉ ቀርባ ወደ ምታገለግልበት ቸርች ለመጎተት ይጠቅማት ዘንድ ታጠምድበታለች። (በዚህ ወጥመዷ የተጠለፉ ጥቂት ሙስሊም ሴቶች እንዳሉ ሰምቻለሁ) ሁለትም የቸርቹ ፕሮግራም በቲቪ በሚተላለፍበት ጊዜ ካሜራ ፊት ሙስሊም መስላ ትታያለች ከፍ ሲልም ትተውናለት።

በዚህ ሁሉ የልጅቱ ማጭበርበር ውስጥ ግን ብቻዋን አይደለችም። የልጅቱ የስራ ድርሻዋ የተሰጣትን ስክሪፕት በብቃት መተወን ብቻ ነው። በገንዘብም ሆነ እቅድ ነድፎ በመስጠት ግን ከጀርባዋ ተኝተው የማያድሩት አክፍሮት ኃላት አሉ። ተመልከቱ እንግዲህ አክፍሮት ኃይላት ሙስሊሙን ለማጥመድ ምን ያህል ርቀው እንደተጓዙና ዓይነቱን እየቀያየሩ ወጥመድ እንደሚያጠምዱ? ምን ያህል ሴቶችን ሒጃብ እያስለበሱ በትነው ይሆን? ምን ያህል ሙስሊሞችስ በነዚህ ወጥመዶች ተጠልፈው ይሆን?

አላህ በሒክማው ከወጥመዳቸው ይጠብቀን!

https://t.me/Zelebet