Get Mystery Box with random crypto!

የበረሀው አንበሳ ሙጃሂድ ሊብያዊው ጀግና ሙጃሂድ ዑመር ሙኽታር በቅኝ ገዢዋ ጣልያን ተይዘው ዳኛው | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

የበረሀው አንበሳ ሙጃሂድ

ሊብያዊው ጀግና ሙጃሂድ ዑመር ሙኽታር በቅኝ ገዢዋ ጣልያን ተይዘው ዳኛው ፊት ቀረቡና ይጠየቁ ጀመር

ዳኛው፦ ጣሊያንን ተዋግተሃል?
ዑመር፦ አዎ
ዳኛው፦ እናም ሰዎች እንዲዋጉ አበረታተሀል?
ዑመር፦ አዎ
ዳኛው፦ የዚህን ድርጊት ቅጣት ያውቃለህ?
ዑመር፦ አዎ
ዳኛው፦ ለስንት ዓመታት ነው የጣሊያን ባለሥልጣናትን የተዋጋሀው?
ዑመር፦ ለ20 ዓመታት በላይ
ዳኛው፦ በሠራኸው ነገር ትጸጸታለህ?
ዑመር፦ በፍፁም
ዳኛው፦ እንደምትገደል ታውቃለህ?
ዑመር፦ አዎ
ዳኛው ሸኽ ዑመር ሙኽታርን ሊደልላቸው ፈለገና እንዲህ አላቸው
ዳኛው፦ ይህ የአንተ መጨረሻ ነው። ለሙጃሂዶች በጣሊያኖች ላይ ጀሀድ እንዲያቆሙ ደብዳቤ ፃፍላቸውና ምህረት ላድርግልህ።
ዑመር ሙኽታር ዳኛውን በቱክረት ተመለከቱትና እንዲህ አሉት በቀን አምስት ጊዜ በሰላት ወቅት ከአላህ በስተቀር አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የእርሱ መልዕክተኛ እንደሆነ የምትመሰክረው ጣቴ የሐሰት ቃል መፃፍ አይቻላትም።

አላህ ገዳዮች ጨቋኞች ፊት እንኳን ቢሆን እውነት ከመናገር የማናፈገፍግ ጀግና ያድርገን!
#OmerMukhtar##ሙጃሂድ

https://t.me/Zelebet