Get Mystery Box with random crypto!

بسم الله الرحمن الرحيم በአንድ መቶ ብር መስጂድ በመገንባት በጀነት ቤትዎን ይገንቡ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

بسم الله الرحمن الرحيم
በአንድ መቶ ብር መስጂድ በመገንባት በጀነት ቤትዎን ይገንቡ

የተከበራችኹ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መዲና ተሰደው እንደገቡ ሙስሊሙን ማሕበረሰብ ለማሰባሰብና በኢስላማዊ ማንነት ለማነጽ በመጀመሪያ የገነቡት መስጂድ እንደኾነ ልብ ይሏል፡፡ መስጂድ ስለመገንባት ትሩፋት መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲናገሩ “መስጂድን የገነባ አላህ አምሳያውን በጀነት ይገነባለታል” ብለዋል፡፡ አላህም (ሱብሓነሁ ወተዓላ) በቃሉ “ የኣላህን መስጂድ የሚቆረቁሩ በኣላህና በመጨረሻው ቀን ያመኑ፣ሰላትንም ያቋቋሙና ዘካትንም የሚሰጡ ከኣለህም ውጪ ማንንም የማይፈሩ ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ከተመሩት ሊኾኑ ይከጀላል” በማለት የኣላህን ቤት መገንባት ያለውን ላቅ ያለ ምንዳ ይነግረናል፡፡
ከዚህም አኳያ እነሆ ይህንን ምንዳ ልናገኝ የምንችልበት ምርጥና ቀላል እድል ከፊታችን ቆሞ እየጠበቀን ነው፡፡ ይኸውም ለመስጂድና መርከዝ መገንቢያ የሚኾን ሰፊ መሬት ሕጋዊ በኾነ መልኩ ለመግዛት ተዋውለን ክፍያውን በተወሰነ መልኩ የፈጸምን ሲኾን ሙሉ በሙሉ ክፍያውን ጨርሶ መሬቱን ለመረከብ አንድ ሚሊየን ኹለት መቶ ሺሕ (1.2 ሚሊየን) ብር ብቻ ይቀርብናል፡፡ ይህ ደግሞ አስራ ኹለት ሺሕ ሰዎች እያንዳንዳቸው አንድ መቶ የኢትጵያ ብር ብቻ ቢያወጡ የሚያጠናቅቁት እጅግ በጣም ትንሽ ገንዘብ ነው፡፡ ኣላህ በመልካም ነገር ተሸቀዳደሙ ስላለን እርሶ አንድ መቶ ብር ብቻ በማውጣት ከነዚያ አስራ ኹለት ሺህ ሰዎች መካከል ይኾናሉ ብለን እንከጅላለን፡፡
ልብ ይበሉ በነፍስ ወከፍ አንድ መቶ ብር ብቻ!!! ከስር ባለው የንግድ ባንክ አካውንት በማስገባት የምንዳው ተጋሪ ይኹኑ፡፡

አበዱ እንድሪስና አብዱ ሶመድ ኡመር
1000441097844